ከዚያም ሄደ፤ የሣፋጥንም ልጅ ኤልሳዕን በዐሥራ ሁለት ጥማድ በሬዎች ሲያርስ፥ እርሱም ከዐሥራ ሁለተኛው ጋር ሆኖ አገኘው። ኤልያስም ወደ እርሱ አልፎ መጐናጸፊያውን ጣለበት።
1 ሳሙኤል 28:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም፥ “ምን አየሽ?” አላት። እርስዋም፥ “ቀጥ ያለ ሽማግሌ ሰው ከምድር ወጣ፤ መጐናጸፊያም ተጐናጽፎአል” አለች። ሳኦልም ሳሙኤል እንደ ሆነ ዐወቀ፤ በፊቱም ወደ ምድር ጐንበስ ብሎ ሰገደለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም፣ “ምን ይመስላል?” ሲል ጠየቃት። እርሷም፣ “ካባ የለበሰ አንድ ሽማግሌ ሰው እየወጣ ነው” አለችው። ሳኦልም ሴትዮዋ ያየችው ሳሙኤል መሆኑን ዐወቀ፤ በመሬትም ላይ ተደፍቶ እጅ ነሣ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም፥ “መልኩ ምን ይመስላል?” ሲል ጠየቃት። እርሷም፥ “ካባ የለበሰ አንድ ሽማግሌ ሰው እየወጣ ነው” አለችው። ሳኦልም ሴትዮዋ ያየችው ሳሙኤል መሆኑን ዐወቀ፤ በመሬትም ላይ ተደፍቶ እጅ ነሣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱም “መልኩ ምንን ይመስላል?” ሲል ጠየቃት። እርስዋም “እነሆ፥ ካባ የለበሰ አንድ ሽማግሌ ሰው እየተነሣ ነው” ስትል መለሰችለት። ሳኦልም ያ ሳሙኤል መሆኑን ዐውቆ ስለ ክብሩ በመሬት ላይ ለጥ ብሎ እጅ ነሣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም፦ መልኩ ምን ዓይነት ነው? አላት። እርስዋም፦ ሽማግሌ ሰው ወጣ፥ መጎናጸፊያም ተጎናጽፎአል አለች። ሳኦልም ሳሙኤል እንደ ሆነ አወቀ፥ በፊቱም ተጎነበሰ፥ በምድርም ላይ እጅ ነሣ። |
ከዚያም ሄደ፤ የሣፋጥንም ልጅ ኤልሳዕን በዐሥራ ሁለት ጥማድ በሬዎች ሲያርስ፥ እርሱም ከዐሥራ ሁለተኛው ጋር ሆኖ አገኘው። ኤልያስም ወደ እርሱ አልፎ መጐናጸፊያውን ጣለበት።
ኤልያስም መጠምጠሚያውን ወስዶ ጠቀለለው፤ የዮርዳኖስንም ውኃ መታበት፤ ውኃውም ወዲህና ወዲያ ተከፈለ፤ ሁለቱም በደረቅ ተሻገሩ። ወጥተውም በምድረ በዳው ቆሙ።
ዳዊትም በዚህ ቃል ሰዎቹን ከለከላቸው። በሳኦልም ላይ ተነሥተው ይገድሉት ዘንድ አልፈቀደላቸውም፤ ሳኦልም ከዋሻው ተነሥቶ መንገዱን ሄደ።