በነጋም ጊዜ እነሆ ልያ ነበረች፤ ያዕቆብም ላባን፥ “ምነው እንደዚህ አደረግህብኝ? ያገለገልሁህ ስለ ራሔል አልነበረምን? ለምን አታለልኸኝ?” አለው።
1 ሳሙኤል 28:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሴቲቱም ሳሙኤልን ባየች ጊዜ በታላቅ ድምፅ ጮኸች፤ ሴቲቱም ሳኦልን፥ “አንተ ሳኦል ስትሆን ለምን አታለልኸኝ?” ብላ ተናገረችው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሴትዮዋም ሳሙኤልን ባየችው ጊዜ በታላቅ ድምፅ ጮኸች፤ ሳኦልንም፣ “አንተ ሳኦል ሆነህ ሳለ፣ ለምን አታለልኸኝ?” አለችው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሴትዮዋም ሳሙኤልን ባየችው ጊዜ በታልቅ ድምፅ ጮኽች፤ ሳኦልንም፥ “አንተ ሳኦል ሆነህ ሳለ፥ ለምን አታለልኸኝ?” አለችው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርስዋም ሳሙኤልን ባየችው ጊዜ ድምፅዋን ከፍ አድርጋ በመጮኽ “ስለምን አታለልከኝ? አንተ ንጉሥ ሳኦል ነህ!” አለችው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሴቲቱም ሳሙኤልን ባየች ጊዜ በታላቅ ድምፅ ጮኸች፥ ሴቲቱም ሳኦልን፦ አንተ ሳኦል ስትሆን ለምን አታለልኸኝ? ብላ ተናገረችው። |
በነጋም ጊዜ እነሆ ልያ ነበረች፤ ያዕቆብም ላባን፥ “ምነው እንደዚህ አደረግህብኝ? ያገለገልሁህ ስለ ራሔል አልነበረምን? ለምን አታለልኸኝ?” አለው።
እግዚአብሔርም አኪያን፥ “እነሆ፥ ስለ ታመመው ልጅዋ ትጠይቅህ ዘንድ የኢዮርብዓም ሚስት ትመጣለች፤ ራስዋንም ለውጣ ወደ አንተ በገባች ጊዜ እንዲህና እንዲህ በላት” አለው።
ሳሙኤል ግን ሞቶ ነበር፤ እስራኤልም ሁሉ አልቅሰውለት ነበር፤ በከተማውም በአርማቴም ቀብረውት ነበር። ሳኦልም መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችን ከምድር አጥፍቶ ነበር።