La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ሳሙኤል 27:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ዳዊት እን​ዲህ አደ​ረገ፤ በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ሀገር በሚ​ቀ​መ​ጥ​በት ዘመን ሁሉ ልማዱ ይህ ነበረ ብለው እን​ዳ​ይ​ና​ገ​ሩ​ብን ብሎ ዳዊት ወደ ጌት ያመ​ጣ​ቸው ዘንድ ወን​ድም ሆነ ሴትም ሆነ ማን​ንም በሕ​ይ​ወት አል​ተ​ወም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ዳዊት “ ‘እርሱ እንዲህ አድርጓል’ ብለው ይነግሩብናል” ብሎ ስላሰበ፣ ወንድም ሆነ ሴት በሕይወት አስቀርቶ ወደ ጋት አላመጣም። በፍልስጥኤም ግዛት በኖረበት ዘመን ሁሉ፣ እንዲህ ማድረጉ የተለመደ ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ዳዊት “ ‘እርሱ እንዲህ አድርጓል’ ብለው ይነግሩብናል” ብሎ ስላሰበ፥ ወንድም ሆነ ሴት በሕይወት አስቀርቶ ወደ ጋት አላመጣም። በፍልስጥኤም ግዛት በኖረበት ዘመን ሁሉ እንዲህ ማድረጉ የተለመደ ነበር።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ዳዊት ወንድንም ሆነ ሴትን ወደ ጋት ሳያመጣ ሁሉንም ገደለ። ይህንንም ያደረገው ዳዊት ይህንንና ይህንን አደረገ ብለው እንዳይነግሩበት ነው። በፍልስጥኤም አገር በኖረበት ዘመን ሁሉ ይህን የማድረግ ልማድ ነበረው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ዳዊት እንዲህ አደረገ በፍልስጥኤማውያንም አገር በሚቀመጥበት ዘመን ሁሉ ልማዱ ይህ ነበረ ብለው እንዳይናገሩብን ብሎ ዳዊት ወደ ጌት ያመጣቸው ዘንድ ወንድም ሆነ ሴትም ሆነ ማንንም በሕይወት አልተወም።

Ver Capítulo



1 ሳሙኤል 27:11
7 Referencias Cruzadas  

የጻድቃን ከንፈሮች ምስክርነትን ያቀናሉ፥ የሚቸኩል ምስክር ግን ክፉ አንደበት አለው።


እስ​ማ​ኤል ማንም ሳያ​ውቅ ጎዶ​ል​ያ​ስን ከገ​ደለ በኋላ በሁ​ለ​ተ​ኛው ቀን እን​ዲህ ሆነ፤


ዳዊት አብ​ያ​ታ​ርን፦ ሶር​ያ​ዊው ዶይቅ በዚያ መኖ​ሩን ባየሁ ጊዜ፥ “ለሳ​ኦል በር​ግጥ ይነ​ግ​ራል ብዬ በዚያ ቀን አው​ቄ​ዋ​ለሁ፤ ለአ​ባ​ትህ ቤት ነፍስ ሁሉ ጥፋት በደ​ለ​ኛው እኔ ነኝ።


አን​ኩ​ስም ዳዊ​ትን፥ “ዛሬ በማን ላይ ዘመ​ታ​ችሁ?” አለው፤ ዳዊ​ትም፥ “በይ​ሁዳ ደቡብ፥ በያ​ሴ​ሜጋ ደቡብ፥ በቄ​ኔ​ዛ​ው​ያን ደቡብ ላይ ዘመ​ትን” አለው።


አን​ኩ​ስም፥ “በሕ​ዝቡ በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ እጅግ የተ​ጠላ ሆኖ​አል፤ ስለ​ዚ​ህም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ባሪያ ይሆ​ነ​ኛል” ብሎ ዳዊ​ትን አመ​ነው።


ሴቶ​ቹ​ንና በው​ስ​ጥ​ዋም የነ​በ​ሩ​ትን ሁሉ ከታ​ናሽ እስከ ታላቅ ድረስ ማር​ከው ነበር፤ ሁሉ​ንም ወስ​ደው መን​ገ​ዳ​ቸ​ውን ሄዱ እንጂ ሴቶ​ች​ንም ሆነ ወን​ዶ​ችን አል​ገ​ደ​ሉም።