በዚያ ዘመን አቤሜሌክ፥ ሚዜው አኮዘትና የሠራዊቱ አለቃ ፋኮል ወደ አብርሃም ሄደው አሉት፥ “በምታደርገው ሁሉ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነው፤
1 ሳሙኤል 24:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁን እንግዲህ ከእኔ በኋላ ዘሬን እንዳትነቅል ከአባቴም ቤት ስሜን እንዳታጠፋው በእግዚአብሔር ማልልኝ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊትም ለሳኦል ማለለት፤ ከዚያም ሳኦል ወደ ቤቱ ተመለሰ። ዳዊትና ሰዎቹ ግን ወደ ዐምባው ወጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዘሮቼን እንዳታጠፋ ስሜንም ከአባቴ ቤት እንዳትደመስስ አሁን በጌታ ማልልኝ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊትም ይህን እንደሚያደርግ ማለለት። ከዚህ በኋላም ሳኦል ወደ ቤቱ ተመልሶ ሄደ፤ ዳዊትና ተከታዮቹም ወደሚሸሸጉበት ስፍራ ተመለሱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም ለሳኦል ማለለት፥ ሳኦልም ወደ ቤቱ ሄደ፥ ዳዊትና ሰዎቹም ወደ አምባው ወጡ። |
በዚያ ዘመን አቤሜሌክ፥ ሚዜው አኮዘትና የሠራዊቱ አለቃ ፋኮል ወደ አብርሃም ሄደው አሉት፥ “በምታደርገው ሁሉ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነው፤
አሁንም በእኔም፥ በልጄም፥ በወገኔም፥ ከእኔም ጋር ባለ ክፉ እንዳታደርግብኝ በእግዚአብሔር ማልልኝ፤ ነገር ግን በእንግድነት መጥተህ ለአንተ ቸርነት እንዳደረግሁ አንተም ለእኔ፥ ለተቀምጥህባትም ምድር ቸርነትን ታደርጋለህ።”
ከልጆቹ ሰባት ሰዎች ስጠንና ከእግዚአብሔር በተመረጠው በሳኦል ሀገር በገባዖን ለእግዚአብሔር እንሠቅላቸዋለን።” ንጉሡም፥ “እሰጣችኋለሁ” አለ።
ንጉሡም በእነርሱ መካከል፥ በዳዊትና በሳኦል ልጅ በዮናታን መካከል ስለ ነበረው ስለ እግዚአብሔር መሐላ የሳኦልን ልጅ የዮናታንን ልጅ ሜምፌቡስቴን ራራለት።
ሳኦልም ዳዊትን፥ “ልጄ ዳዊት ሆይ! ቡሩክ ሁን፤ ማድረግን ታደርጋለህ፤ መቻልንም ትችላለህ” አለው። ዳዊትም መንገዱን ሄደ፤ ሳኦልም ወደ ስፍራው ተመለሰ።