ዳዊትም ከእርሱ ጋር በኢየሩሳሌም ያሉትን አገልጋዮቹን ሁሉ፥ “ተነሡ እንሽሽ፤ ከአቤሴሎም እጅ የምንድንበት የለንምና፤ ፈጥኖ እንዳይዘን፥ ክፉም እንዳያመጣብን፤ ከተማዪቱንም በሰልፍ ስለት እንዳይመታ ፈጥናችሁ እንሂድ” አላቸው።
1 ሳሙኤል 23:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳኦልና ሰዎቹም በተራራው በአንድ ወገን ሄዱ፤ ዳዊትና ሰዎቹም በተራራው በሌላው ወገን ሄዱ። ዳዊትም ከሳኦል ፊት ያመልጥ ዘንድ ተሰውሮ ነበር። ሳኦልና ሰዎቹ ዳዊትንና ሰዎቹን ለመያዝ ከብበዋቸው ነበርና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳኦል በተራራው በአንዱ በኩል ሆኖ ሲያሳድድ፣ ዳዊትና ሰዎቹ ደግሞ በተራራው በሌላ በኩል ከሳኦል ለማምለጥ ይጣደፉ ነበር። ሳኦልና ወታደሮቹ ዳዊትንና ሰዎቹን ከብበው ለመያዝ ተቃርበው ሳሉ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳኦል በተራራው በአንዱ በኩል ሆኖ ሲያሳድድ፥ ዳዊትና ሰዎቹ ደግሞ በተራራው በሌላ በኩል ከሳኦል ለማምለጥ ይጣደፉ ነበር። ሳኦልና ወታደሮቹ ዳዊትንና ሰዎቹን ከበው ለመያዝ ተቃርበው ሳሉ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳኦልና ወታደሮቹ ከኮረብታው በአንድ በኩል ሲሆኑ፥ ዳዊትና ተከታዮቹም ከኮረብታው በሌላ በኩል ነበሩ፤ ዳዊትና ተከታዮቹም ሊማርኩአቸው ከተቃረቡት ከሳኦልና ከወታደሮቹ ለማምለጥ በመጣደፍ ላይ ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳኦልም በተራራው በአንድ ወገን ሄደ፥ ዳዊትና ሰዎቹም በተራራው በሌላው ወገን ሄዱ። ሳኦልና ሰዎቹም ዳዊትንና ሰዎቹን ለመያዝ ከብበዎቸው ነበርና ዳዊት ከሳኦል ፊት ያመልጥ ዘንድ ፈጠነ። |
ዳዊትም ከእርሱ ጋር በኢየሩሳሌም ያሉትን አገልጋዮቹን ሁሉ፥ “ተነሡ እንሽሽ፤ ከአቤሴሎም እጅ የምንድንበት የለንምና፤ ፈጥኖ እንዳይዘን፥ ክፉም እንዳያመጣብን፤ ከተማዪቱንም በሰልፍ ስለት እንዳይመታ ፈጥናችሁ እንሂድ” አላቸው።
አምላካችን ሆይ፥ አንተ አትፈርድባቸውምን? ይህን የመጣብንን ታላቅ ወገን መቃወም እንችል ዘንድ ኀይል የለንም፤ የምናደርግባቸውንም አናውቅም፤ ነገር ግን ዐይኖቻችን ወደ አንተ ናቸው።”
ወንድሞቻችን ሆይ፥ በእስያ መከራ እንደ ተቀበልን ልታውቁ እወዳለሁ፤ ለሕይወታችን ተስፋ እስክንቈርጥ ድረስ ከዐቅማችን በላይ እጅግ መከራ ጸንቶብን ነበርና።
ለጋዛ ሰዎችም፥ “ሶምሶን ወደዚህ መጥቶአል” ብለው ነገሩአቸው፤ ከበቡትም። ሌሊቱንም ሁሉ በከተማዪቱ በር ሸመቁበት፥ “ማለዳ እንገድለዋለን” ብለውም ሌሊቱን ሁሉ በዝምታ ተቀመጡ።
ዮናታንም ደግሞ፥ “ቶሎ ፍጠን፤ አትቈይ” ብሎ ወደ ብላቴናው ጮኸ፤ የዮናታንም ብላቴና ፍላጻዎቹን ሰብስቦ ወደ ጌታው መጣ።
ሳኦልና ሰዎቹም ሊፈልጉት ሄዱ፤ ለዳዊትም ነገሩት፤ እርሱም በማዖን ምድረ በዳ ወዳለው ዓለት ወረደ፤ ሳኦልም ያን በሰማ ጊዜ ዳዊትን በማዖን ምድረ በዳ ተከትሎ አሳደደው።