የሶርያም ንጉሥ መንፈስ ስለዚህ እጅግ ተበሳጨች፤ አገልጋዮቹንም ጠርቶ፥ “ለእስራኤል ንጉሥ ማን እንደሚነግረው አትነግሩኝምን?” አላቸው።
1 ሳሙኤል 22:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁላችሁ በላዬ ዶልታችሁ ተነሣችሁብኝ፤ ልጄ ከእሴይ ልጅ ጋር ሲማማል ማንም አልገለጠልኝም፤ ከእናንተም አንድ ለእኔ የሚያዝን የለም፤ ዛሬም እንደ ሆነው ሁሉ ልጄ አገልጋዬን እንዲዶልት ሲያስነሣብኝ ማንም አላስታወቀኝም” አላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእኔ ላይ የዶለታችሁት ለዚህ ነውን? ልጄ ከእሴይ ልጅ ጋራ ቃል ኪዳን ሲያደርግ ማንም አልነገረኝም፤ ዛሬ እንደሚያደርገው ሁሉ፣ ልጄ አገልጋዬን በእኔ ላይ እንዲያደባብኝ ማነሣሣቱን ከእናንተ ስለ እኔ ተቈርቍሮ የነገረኝ ማንም የለም።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእኔ ላይ የዶለታችሁት ለዚህ ነውን? ልጄ ከእሴይ ልጅ ጋር ቃል ኪዳን ሲያደርግ ማንም አልነገረኝም፤ ዛሬ እንደሚያደርገው ሁሉ፥ ልጄ አገልጋዬን በእኔ ላይ እንዲያደባብኝ ማነሣሣቱን ከእናንተ ስለ እኔ ተቆርቆሮ የነገረኝ ማንም የለም።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእኔስ ላይ ሤራ የምታካሄዱት ስለዚህ ነውን? የገዛ ልጄ ከእሴይ ልጅ ጋር መተባበሩን የነገረኝ ከእናንተ አንድ እንኳ የለም፤ ስለ እኔ የሚያስብ ከቶ ማንም የለም፤ ወይም ዛሬ እንደሚያደርገው ሁሉ አገልጋዬ በእኔ ላይ እንዲሸምቅ ልጄ ያነሣሣው መሆኑን ከእናንተ ማንም የነገረኝ የለም።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁላችሁ በላዬ ዶልታችሁ ተነሣችሁብኝ፥ ልጄ ከእሴይ ልጅ ጋር ሲማማል ምንም አይገልጥልኝም፥ ከእናንተም አንድ ለእኔ የሚያዝን የለም፥ ዛሬም እንደ ሆነው ሁሉ ልጄ ባሪያዬን እንዲዶልት ሲያስነሣብኝ ማንም አላስታወቀኝም አላቸው። |
የሶርያም ንጉሥ መንፈስ ስለዚህ እጅግ ተበሳጨች፤ አገልጋዮቹንም ጠርቶ፥ “ለእስራኤል ንጉሥ ማን እንደሚነግረው አትነግሩኝምን?” አላቸው።
እንዲህም ሆነ፤ ዳዊት ለሳኦል መንገሩን በፈጸመ ጊዜ የዮናታን ነፍስ በዳዊት ነፍስ ታሰረች፤ ዮናታንም እንደ ነፍሱ ወደደው።
ዮናታንም፥ “ይህንስ ያርቀው፤ አትሞትም፤ እነሆ፥ አባቴ አስቀድሞ ለእኔ ሳይገልጥ ትልቅም ሆነ ትንሽ ነገር ቢሆን አያደርግም፤ አባቴስ ይህን ነገር ለምን ይሰውረኛል? እንዲህ አይደለም” አለው።
ዮናታንም ዳዊትን፥ “በሰላም ሂድ፤ እነሆ፥ እኛ ሁለታችን በእኔና በአንተ፥ በዘሬና በዘርህ መካከል እግዚአብሔር ለዘለዓለም ምስክር ይሁን ብለን በእግዚአብሔር ስም ተማምለናል” አለው። ዳዊትም ተነሥቶ ሄደ፤ ዮናታንም ወደ ከተማ ገባ።
እንግዲህ የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ከባሪያህ ጋር አድርገሃልና ለባሪያህ ቸርነትን አድርግ፤ በደል ግን ቢገኝብኝ አንተ ግደለኝ፤ ለምን ወደ አባትህ ታደርሰኛለህ?”
ሳኦልም፥ “አንተ ከእሴይ ልጅ ጋር ለምን ዶለትህብኝ? እንጀራና ሰይፍ ሰጠኸው፤ ዛሬም እንደ ተደረገው ጠላት ሆኖ ይነሣብኝ ዘንድ እግዚአብሔርን ስለ እርሱ ጠየቅህለት” አለው።