1 ሳሙኤል 22:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳኦልም በአጠገቡ የቆሙትን ብላቴኖች፥ “ብንያማውያን ሆይ! እንግዲህ ስሙ በእውነት የእሴይ ልጅ እርሻና የወይን ቦታ ለሁላችሁ ይሰጣችኋልን? ሁላችሁንስ መቶ አለቆችና ሻለቆች ያደርጋችኋልን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳኦልም እንዲህ አላቸው፤ “እናንተ የብንያም ሰዎች ስሙ! በውኑ የእሴይ ልጅ ዕርሻና የወይን ቦታ ለሁላችሁ ይሰጣችኋልን? ሁላችሁንስ ሻለቆችና የመቶ አለቆች ያደርጋችኋልን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳኦልም እንዲህ አላቸው፤ “እናንት የብንያም ሰዎች ስሙ! በውኑ የእሴይ ልጅ እርሻና የወይን ቦታ ለሁላችሁ ይሰጣችኋልን? ሁላችሁንስ ሻለቆችና የመቶ አለቆች ያደርጋችኋልን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳኦልም ባለሟሎችን እንዲህ አላቸው፤ “እናንተ የብንያም ሰዎች አድምጡኝ! በውኑ የእሴይ ልጅ ዳዊት ለሁላችሁም ለእያንዳንዳችሁ የእርሻ መሬትና የወይን ተክል ቦታ የሚሰጣችሁና በሠራዊቱም ውስጥ ሻለቆችና የመቶ አለቆች አድርጎ የሚሾማችሁ ይመስላችኋልን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳኦልም በአጠገቡ የቆሙትን ባሪያዎቹን፦ ብንያማውያን ሆይ፥ እንግዲህ ስሙ፥ በውኑ የእሴይ ልጅ እርሻና የወይን ቦታ ለሁላችሁ ይሰጣችኋልን? ሁላችሁንስ ሻለቆችና የመቶ አለቆች ያደርጋችኋልን? |
በዚያም አንድ ብንያማዊ የቢኮሪ ልጅ ስሙ ሳቡሄ የሚባል የዐመፅ ልጅ የሆነ ሰው ነበረ፤ እርሱም፥ “ከዳዊት ዘንድ እድል ፋንታ የለንም፦ ከእሴይም ልጅ ዘንድ ርስት የለንም፤ እስራኤል ሆይ፥ እያንዳንድህ ወደ ድንኳንህ ተመለስ” ብሎ መለከት ነፋ።
እስራኤልም ሁሉ ንጉሡ እንዳልሰማቸው ባዩ ጊዜ ሕዝቡ ለንጉሡ፥ “በዳዊት ዘንድ ምን ክፍል አለን? በእሴይም ልጅ ዘንድ ርስት የለንም። እስራኤል ሆይ፥ ወደ ድንኳኖቻችሁ ተመለሱ፤ ዳዊት ሆይ፥ አሁን የራስህን ቤት ተመልከት” ብለው መለሱለት። እስራኤልም ወደየቤታቸው ተመለሱ።
በዚያም ቀን የእሴይ ሥር ይቆማል፤ የተሾመውም የአሕዛብ አለቃ ይሆናል፤ አሕዛብም በእርሱ ተስፋ ያደርጋሉ፤ ማረፊያውም የተከበረ ይሆናል።
ከመባቻም በኋላ በማግሥቱ በሁለተኛው ቀን የዳዊት ስፍራ ባዶውን ነበረ፤ ሳኦልም ልጁን ዮናታንን፥ “የእሴይ ልጅ ትናትና ዛሬ ወደ ግብር ያልመጣ ስለምን ነው?” አለው።
ሳኦልም በዮናታን ላይ እጅግ ተቈጣ፥ “አንተ የከዳተኞች ሴቶች ልጅ! የእሴይን ልጅ ለአንተ ማፈርያ፥ ለእናትህም ኀፍረተ ሥጋ ማፈርያ እንደ መረጥህ እኔ አላውቅምን?
ሳኦልም፥ “አንተ ከእሴይ ልጅ ጋር ለምን ዶለትህብኝ? እንጀራና ሰይፍ ሰጠኸው፤ ዛሬም እንደ ተደረገው ጠላት ሆኖ ይነሣብኝ ዘንድ እግዚአብሔርን ስለ እርሱ ጠየቅህለት” አለው።
የሳኦልም በቅሎዎች ጠባቂ ሶርያዊው ዶይቅ መልሶ፥ “የእሴይ ልጅ ወደ ኖብ ወደ አኪጦብ ልጅ ወደ ካህኑ አቤሜሌክ ሲመጣ አይቼዋለሁ።
ናባልም ተነሥቶ ለዳዊት ብላቴኖች መለሰላቸው እንዲህም አላቸው፥ “ዳዊት ማን ነው? የእሴይስ ልጅ ማን ነው? እያንዳንዳቸው ከጌቶቻቸው የኰበለሉ አገልጋዮች ዛሬ ብዙ ናቸው።