1 ሳሙኤል 22:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሞዓብንም ንጉሥ ማለደው፤ ዳዊትም በአንባ ውስጥ በነበረበት ወራት ሁሉ በእርሱ ዘንድ ተቀመጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም በሞዓብ ንጉሥ ዘንድ አስቀመጣቸው፤ ዳዊት በዐምባ ውስጥ እስከ ቈየበትም ጊዜ ድረስ ከንጉሡ ዘንድ ተቀመጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም በሞዓብ ንጉሥ ዘንድ አስቀመጣቸው፤ ዳዊት በዐምባ ውስጥ እስከቆየበትም ጊዜ ድረስ ከንጉሡ ዘንድ ተቀመጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህም ዐይነት ወላጆቹን በሞአብ ንጉሥ ዘንድ ተዋቸው፤ እነርሱም ዳዊት እየተደበቀ በሚኖርበት ዘመን ሁሉ በዚያው ቈዩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሞዓብም ንጉሥ ፊት አመጣቸው፥ ዳዊትም በአምባ ውስጥ በነበረበት ወራት ሁሉ በእርሱ ዘንድ ተቀመጡ። |
ዳዊትም ሞዓባውያንን መታ፤ በምድርም ጥሎ በገመድ ሰፈራቸው፤ በሁለትም ገመድ ለሞት፥ በአንድም ገመድ ለሕይወት ሰፈራቸው፤ ሞዓባውያንም ለዳዊት ገባሮች ሆኑ፤ ግብርም አመጡለት።
የንጉሡም የዳዊት የፊተኛውና የኋለኛው ነገር፥ እነሆ፥ በባለራእዩ በሳሙኤል ታሪክ፥ በነቢዩም በናታን ታሪክ፥ በባለ ራእዩም በጋድ ታሪክ ተጽፎአል።
ይህንም ትእዛዝ እግዚአብሔር በነቢያቱ እጅ አዝዞአልና እንደ ዳዊትና እንደ ንጉሡ ባለ ራእይ እንደ ጋድ፥ እንደ ነቢዩም እንደ ናታን ትእዛዝ፥ ጸናጽልና በገና፥ መሰንቆም አስይዞ ሌዋውያንን በእግዚአብሔር ፊት አቆመ።
በአንዲቱ ከተማም መከራ ቢያሳዩአችሁ ወደ ሌላይቱ ሽሹ፤ እውነት እላችኋለሁና፤ የሰው ልጅ እስኪመጣ ድረስ የእስራኤልን ከተማዎች አትዘልቁም።
ዳዊትም ከዚያ በሞዓብ ምድር ወዳለችው ወደ መሴፋ ሄደ፤ የሞዓብንም ንጉሥ፥ “እግዚአብሔር የሚያደርግልኝን እስካውቅ ድረስ አባቴና እናቴ ከአንተ ጋር ይቀመጡ ዘንድ እለምንሃለሁ” አለው።
ነቢዩ ጋድም ዳዊትን፥ “ተነሥተህ ወደ ይሁዳ ምድር ሂድ እንጂ በአንባው ውስጥ አትቀመጥ” አለው፤ ዳዊትም ሄደ፤ ወደ ሳሬቅ ከተማም መጥቶ ተቀመጠ፤