የተጠሩትም ሁለት መቶ ሰዎች ከአቤሴሎም ጋር ከኢየሩሳሌም ሄዱ፤ እነርሱም በየዋህነት ሄዱ፤ ነገሩንም ሁሉ ከቶ አያውቁም ነበር።
1 ሳሙኤል 22:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በውኑ ስለ እርሱ እግዚአብሔርን እጠይቅ ዘንድ ዛሬ ጀመርሁን? ይህ ከእኔ ይራቅ፤ እኔ ባሪያህ ይህን ሁሉ ትልቅ ወይም ጥቂት ቢሆን አላውቅምና ንጉሡ እንደዚህ ያለውን ነገር በእኔ በባሪያውና በአባቴ ቤት ሁሉ ላይ አያኑር” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለ እርሱ እግዚአብሔርን ስጠይቅስ ያ ቀን የመጀመሪያ ጊዜዬ ነበርን? ፈጽሞ አልነበረም፤ ይህን ጕዳይ በተመለከተ አገልጋይህ የሚያውቀው ምንም ነገር ስለሌለ ንጉሥ እኔን አገልጋዩን ወይም ከአባቴ ቤተ ሰብ ማንንም ጥፋተኛ አያድርግ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለ እርሱ እግዚአብሔርን ስጠይቅስ ያ ቀን የመጀመሪያ ጊዜዬ ነበርን? ፈጽሞ አልነበረም፤ ይህን ጉዳይ በተመለከተ አገልጋይህ የሚያውቀው ምንም ነገር ስለ ሌለ ንጉሥ እኔን አገልጋዩን ወይም ከአባቴ ቤተሰብ ማንንም ጥፋተኛ አያድርግ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በውኑ እግዚአብሔርን ስለ እርሱ መጠየቅ ይህ ዛሬ የመጀመሪያ ጊዜዬ ነውን? አይደለም! ንጉሥ ሆይ! እኔን አገልጋይህንም ሆነ ቤተሰቤን በዚህ ጉዳይ ላይ አትውቀስ፤ ስለዚህ ጉዳይ ይብዛም ይነስም እኔ የማውቀው ነገር የለም።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በውኑ ስለ እርሱ እግዚአብሔርን እጠይቅ ዘንድ ዛሬ ጀመርሁን? ይህ ከእኔ ይራቅ፥ እኔ ባሪያህ ይህን ሁሉ እጅግ ወይም ጥቂት ቢሆን አላውቅምና ንጉሡ እንደዚህ ያለውን ነገር በእኔ በባሪያውና በአባቴ ቤት ሁሉ ላይ አያኑር አለ። |
የተጠሩትም ሁለት መቶ ሰዎች ከአቤሴሎም ጋር ከኢየሩሳሌም ሄዱ፤ እነርሱም በየዋህነት ሄዱ፤ ነገሩንም ሁሉ ከቶ አያውቁም ነበር።
ንጉሡንም የማሻገር ሥራ ሠሩ። የንጉሡንም ቤተ ሰብእ ያነሡ ዘንድ፥ በፊቱም የቀና ሥራን ይሠሩ ዘንድ ወደ ማዶ ተሻገሩ። ንጉሡም ዮርዳኖስን ከተሻገረ በኋላ የጌራ ልጅ ሳሚ በንጉሡ ፊት፦ በግንባሩ ወደቀ።
እርሱም ንጉሡን አለው፥ “ጌታዬ! ኀጢአቴን አትቍጠርብኝ፤ ጌታዬ ንጉሡ ከኢየሩሳሌም በወጣህ ቀን ባሪያህ የበደልሁህን አታስብብኝ፤ ጌታዬ ንጉሡም በልብህ አታኑርብኝ።
ዳዊትም፥ “ወደ ፍልስጥኤማውያን ልውጣን? በእጄስ አሳልፈህ ትሰጣቸዋለህን?” ብሎ እግዚአብሔርን ጠየቀ። እግዚአብሔርም ዳዊትን፥ “ፍልስጥኤማውያንን በርግጥ በእጅህ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁና ውጣ” አለው።
ዳዊትም እግዚአብሔርን ጠየቀ፤ እግዚአብሔርም፥ “በኋላቸው ዞረህ በሾላው ዛፍ ፊት ለፊት ግጠማቸው እንጂ አትውጣ።
በእግዚአብሔር ቸርነትና ይቅርታ መመኪያችንና የነፃነታችን ምስክር ይህቺ ናትና፥ በሥጋዊ ጥበብ ሳይሆን፥ በእግዚአብሔር ጸጋ በዚህ ዓለም፥ ይልቁንም በእናንተ ዘንድ ተመላለስን።
አቤግያም ወደ ናባል መጣች፤ እነሆም፥ በቤቱ እንደ ንጉሥ ግብዣ ያለ ግብዣ ያደርግ ነበር፤ ናባልም እጅግ ሰክሮ ነበርና ልቡ ደስ ብሎት ነበር፤ ስለዚህም እስኪነጋ ድረስ ታናሽ ነገር ወይም ታላቅ ነገር አልነገረችውም ነበር።