1 ሳሙኤል 22:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡም የአኪጦብን ልጅ ካህኑን አቤሜሌክን፥ በኖብም ያሉትን ካህናት፥ የአባቱን ልጆች ሁሉ ልኮ አስጠራቸው፤ ሁላቸውም ወደ ንጉሡ መጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ንጉሡ፣ የአኪጦብን ልጅ ካህኑን አቢሜሌክን፣ በኖብ ካህናት የነበሩትን የአባቱን ቤተ ሰብ በሙሉ ልኮ አስጠራቸው፤ ሁሉም ወደ ንጉሡ መጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ንጉሡ፥ የአኪጦብን ልጅ ካህኑን አቢሜሌክን፥ በኖብ ካህናት የነበሩትን የአባቱን ቤተሰብ በሙሉ ልኮ አስጠራቸው፤ ሁሉም ወደ ንጉሡ መጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም ንጉሥ ሳኦል ወደ ካህኑ የአሒጡብ ልጅ ወደ ሆነው ወደ አቤሜሌክና በኖብ ወደሚገኙት ዘመዶቹ ወደሆኑት ካህናት ሁሉ መልእክት ላከ፤ እነርሱም መጡ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም የአኪጦብን ልጅ ካህኑን አቢሜሌክን በኖብም ያሉትን ካህናት የአባቱን ቤት ሁሉ ልኮ አስጠራቸው፥ ሁላቸውም ወደ ንጉሡ መጡ። |
ዳዊትም ወደ ካህኑ ወደ አቤሜሌክ ወደ ኖብ መጣ፤ አቤሜሌክም እርሱን በተገናኘው ጊዜ ደነገጠ፥ “ስለምን አንተ ብቻህን ነህ? ከአንተስ ጋር ስለምን ማንም የለም?” አለው።