La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ሳሙኤል 22:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ዳዊ​ትም ከዚያ ተነ​ሥቶ አመ​ለጠ፤ ወደ ዔዶ​ላም ዋሻም መጣ፤ ወን​ድ​ሞ​ቹና የአ​ባቱ ቤተ ሰብ ሁሉ ይህን በሰሙ ጊዜ ወደ እርሱ ወደ​ዚያ ወረዱ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ዳዊት ከጌት ወደ ዓዶላም ዋሻ ሸሸ፤ ወንድሞቹና የአባቱ ቤተ ሰቦች ይህን በሰሙ ጊዜ፣ እርሱ ወዳለበት ወደዚያው ወረዱ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ዳዊት ከጋት ተነስቶ ወደ ዓዶላም ዋሻ ሸሸ፤ ወንድሞቹና የአባቱ ቤተሰቦች ይህን በሰሙ ጊዜ፥ እርሱ ወዳለበት ወደዚያው ወረዱ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ዳዊት ከጋት ከተማ ሸሽቶ በዐዱላም ከተማ አጠገብ ወደሚገኝው ወደ አንድ ዋሻ ሄደ፤ ወንድሞቹና ሌሎቹም ቤተሰቦቹ ይህን በሰሙ ጊዜ ወደዚያ ሄደው ከእርሱ ጋር ተቀላቀሉ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ዳዊትም ከዚያ ተነሣ ወደ ዓዶላም ዋሻ ኮበለለ፥ ወንድሞቹና የአባቱም ቤት ሰው ሁሉ ይህን በሰሙ ጊዜ ወደ እርሱ ወደዚያ ወረዱ።

Ver Capítulo



1 ሳሙኤል 22:1
13 Referencias Cruzadas  

በዚ​ያም ወራት እን​ዲህ ሆነ፤ ይሁዳ ከወ​ን​ድ​ሞቹ ተለ​ይቶ ወረደ፤ ስሙ ኤራስ በሚ​ባል በዓ​ዶ​ሎ​ማ​ዊ​ውም ሰው ዘንድ አደረ።


ከሠ​ላ​ሳ​ውም አለ​ቆች ሦስቱ ወር​ደው ዳዊት ወዳ​ለ​በት ወደ ዓለቱ ወደ ዓዶ​ላም ዋሻ መጡ፤ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ጭፍራ በኀ​ያ​ላን ሸለቆ ሰፍሮ ነበር።


አቤቱ፥ የሚ​በ​ድ​ሉ​ኝን በድ​ላ​ቸው፥ የሚ​ዋ​ጉ​ኝ​ንም ተዋ​ጋ​ቸው።


በመሪሳ የምትቀመጪ ሆይ፥ ወራሽ አመጣብሻለሁ፥ የእስራኤል ክብር ወደ ዓዶላም ይመጣል።


እነሆ፥ እግዚአብሔር ከስፍራው ይወጣል፥ ወርዶም በምድር ከፍታዎች ላይ ይረግጣል።


ዓለም የማ​ይ​ገ​ባ​ቸው እነ​ዚህ ናቸው፤ ዱር ለዱ​ርና ተራራ ለተ​ራራ፥ ዋሻ ለዋ​ሻና ፍር​ኩታ ለፍ​ር​ኩ​ታም ዞሩ።


የል​ብና ንጉሥ፥ የዓ​ዶ​ላም ንጉሥ፥


ኤር​ሙት፥ ኤዶ​ላም፥ ሜም​ብራ፥ ሰአክ፥ አዚቃ፤


በመ​ን​ገ​ድም አጠ​ገብ ወዳ​ሉት የበ​ጎች ማደ​ሪ​ያ​ዎች ወጣ፤ በዚ​ያም ዋሻ ነበረ፤ ሳኦ​ልም ወገ​ቡን ይሞ​ክር ዘንድ ወደ​ዚያ ዋሻ ገባ፤ ዳዊ​ትና ሰዎ​ቹም ከዋ​ሻው በው​ስ​ጠ​ኛው ቦታ ተቀ​ም​ጠው ነበር።