እነሆም፦ ሂድ ፍላጻዎቹን ፈልግ ብዬ ብላቴናውን እልካለሁ፤ ብላቴናውንም፦ እነሆ፥ ፍላጻው ከአንተ ወደዚህ ነው፤ ይዘኸው ወደ እኔ ና ያልሁት እንደ ሆነ፥ ሕያው እግዚአብሔርን! ለአንተ ሰላም ነውና ምንም ክፉ ነገር የለብህም።
1 ሳሙኤል 20:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብላቴናውን ግን፦ እነሆ፥ ፍላጻው ከአንተ ወዲያ ነው ያልሁት እንደ ሆነ፥ እግዚአብሔር አሰናብቶሃልና መንገድህን ሂድ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ልጁን፣ ‘እነሆ፤ ፍላጾቹ ያሉት ከአንተ ወዲያ ዐልፎ ነው’ ያልሁት እንደ ሆነ እግዚአብሔር እንድትሄድ ፈቅዷልና ሂድ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ልጁን፥ ‘እነሆ፤ ፍላጾቹ ያሉት ከአንተ ወዲያ ዐልፎ ነው’ ያልሁት እንደሆነ ጌታ እንድትሄድ ፈቅዷልና ሂድ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ልጁን እነሆ! ‘ፍላጻዎቹ ከአንተ ወዲያ ናቸው!’ ያልኩት እንደ ሆነ እግዚአብሔር አሰናብቶሃልና መንገድህን ሂድ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ብላቴናውን ግን፦ እነሆ፥ ፍላጻው ከአንተ ወዲያ ነው ያልሁት እንደ ሆነ፥ እግዚአብሔር አሰናብቶሃልና መንገድህን ሂድ። |
እነሆም፦ ሂድ ፍላጻዎቹን ፈልግ ብዬ ብላቴናውን እልካለሁ፤ ብላቴናውንም፦ እነሆ፥ ፍላጻው ከአንተ ወደዚህ ነው፤ ይዘኸው ወደ እኔ ና ያልሁት እንደ ሆነ፥ ሕያው እግዚአብሔርን! ለአንተ ሰላም ነውና ምንም ክፉ ነገር የለብህም።
ብላቴናውም ዮናታን ፍላጻውን ወደ ወረወረበት ስፍራ በመጣ ጊዜ ዮናታን፥ “ፍላጻው ከአንተ ወዲያ ነው” ብሎ ወደ ብላቴናው ጮኸ።
ዮናታንም ዳዊትን፥ “በሰላም ሂድ፤ እነሆ፥ እኛ ሁለታችን በእኔና በአንተ፥ በዘሬና በዘርህ መካከል እግዚአብሔር ለዘለዓለም ምስክር ይሁን ብለን በእግዚአብሔር ስም ተማምለናል” አለው። ዳዊትም ተነሥቶ ሄደ፤ ዮናታንም ወደ ከተማ ገባ።