1 ሳሙኤል 2:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንጀራ ጠግበው የነበሩ ተራቡ፤ ተርበውም የነበሩ ጠገቡ፤ መካኒቱ ሰባት ወልዳለችና፥ ብዙም የወለደችው መውለድ አልቻለችም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጠግበው የነበሩ ለእንጀራ ሲሉ ተገዙ፤ ተርበው የነበሩ ግን እንጀራ ጠገቡ፤ መካኒቱ ሰባት ልጆች ወልዳለች፤ ብዙ ወንዶች ልጆች ወልዳ የነበረችው ግን መከነች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጠግበው የነበሩ አጥተው ለእንጀራ ተገዙ፤ ተርበው የነበሩ ግን ከራብ ዐርፈዋል። መካኒቱ ሰባት ወለደች፥ ብዙ የወለደችው ግን ብቻዋን ቀረች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጠግበው የነበሩ ተርበው ለምግብ ተገዝተዋል፤ ተርበው የነበሩ ግን ጠግበዋል፤ መኻኒቱ ሰባት ወለደች፤ የብዙዎች ልጆች እናት የነበረችው ብቻዋን ቀረች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጠግበው የነበሩ እንጀራ አጡ፥ ተርበው የነበሩ ከራብ ዐርፈዋል፥ መካኒቱ ሰባት ወልዳለችና፥ ብዙም የወለደችው ደክማለች። |
አጥንቶች ሁሉ እንዲህ ይሉሃል፦ “አቤቱ፥ እንደ አንተ ማን ነው? ድሃውን ከሚቀማው እጅ ድሃውንና ችግረኛውንም ከሚነጥቀው እጅ ታድነዋለህ።”
አንቺ ያልወለድሽ መካን ሆይ፥ ደስ ይበልሽ፤ አንቺ ያላማጥሽ ሆይ፥ እልል በዪ፤ ጩኺም፤ ባል ካላት ይልቅ ፈት የሆነቺቱ ልጆች በዝተዋልና፥ ይላል እግዚአብሔር።
ሰባት የወለደች ባዶ ቀረች፤ ነፍስዋም ተጨንቃለች፤ በቀትር ጊዜ ፀሐይዋ ገብታባታለች፤ አፍራለች፤ ተዋርዳማለች፤ የተረፉትንም በጠላቶቻቸው ፊት ለሰይፍ አሳልፌ እሰጣለሁ፥” ይላል እግዚአብሔር።
አብርሃም ግን እንዲህ አለው፦ ‘ልጄ ሆይ፥ አንተ በሕይወትህ ተድላና ደስታ እንዳደረግህ፥ አልዓዛርም እንዲሁ ሁልጊዜ በችጋር እንደ ነበረ ዐስብ፤ አሁን ግን እንዲሁ እርሱ በዚህ ፈጽሞ ተድላና ደስታ ያደርጋል፤ አንተ ግን መከራ ትቀበላለህ።
“የማትወልድ መካን ደስ ይላታል፤ ምጥ የማታውቀውም ደስ ብሎአት እልል ትላለች፤ ባል ካላት ይልቅ የፈቲቱ ልጆች ብዙዎች ናቸውና” ተብሎ ተጽፎአል።
የመውለጃዋም ወራት በደረሰ ጊዜ ሐና ወንድ ልጅ ወለደች፤ እርስዋም፥ “ከሠራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ለምኜዋለሁ” ስትል ስሙን “ሳሙኤል” ብላ ጠራችው።
እንደ መከራዋና እንደ ኀዘንዋም እግዚአብሔር ልጅ አልሰጣትም ነበር። ስለዚህም ታዝን ነበር። እግዚአብሔር ማኅፀንዋን ዘግትዋልና፥ ልጆችንም አልሰጣትምና።