ነገር ግን እስከ ንጉሡ እስከ ኢዮአስ እስከ ሃያ ሦስተኛው ዓመት ድረስ ከመቅደሱ ውስጥ የተናዱትን ካህናቱ አልጠገኑትም ነበር።
1 ሳሙኤል 2:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመሥዋዕቴ ላይና በዕጣኔ ላይ ስለ ምን በክፉ ዐይን ተመለከትህ? የእስራኤል ልጆች በፊቴ ከሚያቀርቡት መሥዋዕት ሁሉ በቀዳምያቱ ስለ አከበርሁህ ከእኔ ይልቅ ልጆችህን ለምን መረጥህ? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ታዲያ በማደሪያዬ እንዲቀርብ ያዘዝሁትን መሥዋዕትና ቍርባን የናቃችሁ ለምንድን ነው? አንተና ልጆችህ ሕዝቤ እስራኤል ካቀረበው ቍርባን ሁሉ ምርጥ ምርጡን በልታችሁ ራሳችሁን በማወፈር ከእኔ ይልቅ ልጆችህን የምታከብራቸው ስለ ምንድን ነው?’ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በማደሪያዬ እንዲያቀርቡት ያዘዝሁትን መሥዋዕቴንና ቁርባኔን ስለምን ረገጣችሁ? ሕዝቤ እስራኤል ካቀረበው ቁርባን ሁሉ ምርጥ ምርጡን በልታችሁ ራሳችሁን በማወፈር፥ ከእኔ ይልቅ ለልጆችህ ስለምን ክብር ሰጠህ?’ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በትእዛዜ መሠረት የሚቀርብልኝን መሥዋዕትና ቊርባን ለምን ታዋርዳላችሁ? ልጆችህ ለመሥዋዕት ከሚቀርበው ምርጥ የሆነውን እየወሰዱ በመብላት ይወፍሩ ዘንድ እነርሱን ከእኔ ይበልጥ የምታከብራቸው ለምንድነው?’ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በማደሪያዬ ያቀርቡት ዘንድ ያዘዝሁትን መሥዋዕቴንና ቍርባኔን ስለ ምን ረገጣችሁ? እንድትወፍሩም የሕዝቤን የእስራኤልን ቍርባን ሁሉ መጀመሪያ በመብላታችሁ ከእኔ ይልቅ ልጆችህን ለምን አከበርህ? |
ነገር ግን እስከ ንጉሡ እስከ ኢዮአስ እስከ ሃያ ሦስተኛው ዓመት ድረስ ከመቅደሱ ውስጥ የተናዱትን ካህናቱ አልጠገኑትም ነበር።
ከንቱ ነገርን ለሚሰሙት ሕዝቤ እየዋሻችሁ ሞት የማይገባቸውን ነፍሳት ትገድሉ ዘንድ፥ በሕይወትም መኖር የማይገባቸውን በሕይወት ታኖሩ ዘንድ ስለ ጭብጥ ገብስና ስለ ቍራሽ እንጀራ ሕዝቤን አርክሳችኋል።
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ በእረኞች ላይ ነኝ፤ በጎችንም ከእጃቸው እፈልጋለሁ፤ በጎችንም ከማሰማራት አስተዋቸዋለሁ፤ ከዚያም ወዲያ እረኞች በጎችን አያሰማሩም፤ በጎችንም ከአፋቸው አድናለሁ፤ መብልም አይሆኑላቸውም።
“የሰው ልጅ ሆይ! ትንቢት ተናገር፤ በእስራኤል እረኞች ላይ ትንቢት ተናገር፤ እረኞችንም እንዲህ በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ራሳቸውን ለሚያሰማሩ ለእስራኤል እረኞች ወዮላቸው! እረኞች ራሳቸውን ያሰማራሉን? እረኞች በጎችን ያሰማሩ ዘንድ አይገባቸውምን?
እግዚአብሔር ሕዝቤን ስለሚያስቱ ነቢያት እንዲህ ይላል፥ በጥርሳቸው ሲነክሱ በሰላም ይሰብካሉ፥ በአፋቸው ግን አንዳች በማይሰጥ ሰው ላይ ሰልፍን ያስቡበታል።
ከእኔ ይልቅ አባቱን ወይም እናቱን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም፤ ከእኔ ይልቅም ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም።
ደቀ ዛሙርታቸውንም ከሄሮድስ ወገን ጋር ላኩበት፤ እነርሱም “መምህር ሆይ! እውነተኛ እንደ ሆንህ በእውነትም የእግዚአብሔርን መንገድ እንድታስተምር እናውቃለን፤ ለማንምም አታደላም፤ የሰውን ፊት አትመለከትምና፤
“ወደ እኔ የሚመጣ፥ ሊከተለኝም የሚወድ አባቱንና እናቱን፥ ሚስቱንና ልጆቹን፥ ወንድሞቹንና እኅቶቹን፥ የራሱንም ሰውነት እንኳ ቢሆን የማይጠላ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም።
እነርሱ ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ያይደለ ለሆዳቸው ይገዛሉና፤ በነገር ማታለልና በማለዛዘብም የብዙዎች የዋሃንን ልብ ያስታሉ፤
ስለዚህ ከአሁን ጀምሮ በሥጋ የምናውቀው የለም፤ ክርስቶስንም በሥጋ ብናውቀው አሁን ግን ከእንግዲህ ወዲህ የምናውቀው አይደለም።
ያዕቆብ በላ፤ ጠገበም፤ የተወደደውን ጥጋብ አቀናጣው፤ ሰባ፥ ወፈረ፥ ሰፋ፤ የፈጠረውንም እግዚአሔርን ተወ፤ ከሕይወቱ ከእግዚአብሔርም ራቀ።
እናቱንና አባቱን አላየኋችሁም ላለ፥ ወንድሞቹንም ላላወቀ፥ ልጆቹንም ላላስተዋለ፤ ቃልህን ለጠበቀ፥ በቃል ኪዳንህም ለተማጠነ።
ላይኛይቱ ጥበብ ግን በመጀመሪያ ንጽሕት ናት፤ በኋላም ታራቂ፥ ገር፥ እሺ ባይ፥ ምሕረትና በጎ ፍሬ የሞላባት፥ ጥርጥርና ግብዝነት የሌለባት ናት።
የእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ በሴሎ ተሰበሰቡ፤ በዚያም የምስክሩን ድንኳን ተከሉ፤ ምድሩም ጸጥ ብሎ ተገዛላቸው።
ልጆቹ በእግዚአብሔር ላይ ክፉ እንዳደረጉ ዐውቆ አልገሠጻቸውምና ስለ ልጆቹ ኀጢአት ለዘለዓለም ቤቱን እንደምበቀል አስታውቄዋለሁ።