1 ሳሙኤል 19:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልብሱንም አወለቀ፤ በፊታቸውም ትንቢት ተናገረ፤ ራቁቱንም ወድቆ በዚያ ቀን ሁሉ በዚያም ሌሊት ሁሉ ተጋደመ። ስለዚህ፥ “ሳኦል ደግሞ ከነቢያት መካከል ነውን?” ይባባሉ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም ልብሱን አውልቆ፣ በሳሙኤልም ፊት ደግሞ ትንቢት ተናገረ፤ በዚህ ሁኔታም ቀኑንና ሌሊቱን በሙሉ ዕራቍቱን ተጋደመ። ሕዝቡ፣ “ሳኦልም ደግሞ ከነቢያት እንደ አንዱ ሆኖ ተቈጠረ?” ያለው በዚህ ምክንያት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም ልብሱን አውልቆ፥ በሳሙኤልም ፊት ደግሞ ትንቢት ተናገረ፤ በዚህ ሁኔታም ቀኑንና ሌሊቱን በሙሉ ራቁቱን ተጋደመ። ሕዝቡ፥ “ሳኦልም ደግሞ ከነቢያት እንደ አንዱ ሆኖ ተቆጠረ?” ካለው የተነሣ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ ሳሙኤልም ፊት ሲቀርብ ልብሱን አውልቆ ትንቢት እየተናገረ፤ ቀኑንም ሌሊቱንም ሁሉ ራቁቱን በዚያው ተጋድሞ ዋለ፤ “ሳኦልም ከነቢያት እንደ አንዱ ሆኖ ተቈጠርን?” የሚለው የምሳሌ አነጋገር የመነጨው ከዚህ የተነሣ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ልብሱንም አወለቀ፥ በሳሙኤልም ፊት ትንቢት ተናገረ፥ ራቁቱንም ወድቆ በዚያ ቀን ሁሉ በዚያም ሌሊት ሁሉ ተጋደመ። ስለዚህ፦ ሳኦል ደግሞ ከነቢያት መካከል ነውን? ይባባሉ ነበር። |
ዳዊትም ቤተ ሰቡን ሊመርቅ ተመለሰ። የሳኦል ልጅ ሜልኮልም ዳዊትን ለመቀበል ወጣችና ሰላምታ ሰጠችው፥ “ከሚዘፍኑት አንዱ እንደሚገለጥ የእስራኤል ንጉሥ በአገልጋዮቹ ሚስቶች ፊት በመገለጡ ምንኛ የተከበረ ነው!” አለች።
በዚያ ዓመት እግዚአብሔር የአሞጽን ልጅ ኢሳይያስን፥ “ሂድ፥ ማቅህን ከወገብህ አውጣ፤ ጫማህንም ከእግርህ አውልቅ፤ ያለጫማም በባዶ እግርህ ሂድ” ብሎ ተናገረው። እንዲህም አደረገ፤ ራቁቱንም ያለ ጫማ ሄደ።
“የእግዚአብሔርን ቃል የሚሰማ፥ ሁሉን የሚችል የአምላክን ራእይ የሚያይ፥ ተኝቶ ዐይኖቹ የተከፈቱለት እንዲህ ይላል፦
የሰሙትም ሁሉ አደነቁ፤ እንዲህም አሉ፥ “በኢየሩሳሌም ይህን ስም የሚጠሩትን ሁሉ ይጠላቸው የነበረው ይህ አይደለምን? ስለዚህ ወደዚህ የመጣው እያሰረ ወደ ሊቀ ካህናቱ ሊወስዳቸው አይደለምን?”
የእግዚአብሔርም መንፈስ በአንተ ይወርዳል፤ ከእነርሱም ጋር ትንቢት ትናገራለህ፤ እንደ ሌላም ሰው ሆነህ ትለወጣለህ።
ሳሙኤልም እስከ ሞተበት ቀን ድረስ ሳኦልን ለማየት ዳግመኛ አልሄደም፤ ሳሙኤልም ለሳኦል አለቀሰ፤ እግዚአብሔርም በእስራኤል ላይ ሳኦልን ስላነገሠ ተጸጸተ።
እንዲህም ሆነ፤ በነጋው ሳኦልን ክፉ መንፈስ ከእግዚአብሔር ዘንድ ያዘው፤ በቤቱም ውስጥ ትንቢት ተናገረ። ዳዊትም በየቀኑ ያደርግ እንደ ነበረ በእጁ በገና ይመታ ነበር። ሳኦልም ጦሩን በእጁ ይዞ ነበር።