1 ሳሙኤል 19:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም ሸሽቶ አመለጠ፤ ወደ አርማቴምም ወደ ሳሙኤል መጣ፤ ሳኦልም ያደረገበትን ሁሉ ነገረው፤ እርሱና ሳሙኤልም ሄዱ፤ በአውቴዘራማም ተቀመጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊት ሸሽቶ ካመለጠ በኋላ፣ ወደ አርማቴም ወደ ሳሙኤል ሄደ፣ ሳኦል ያደረገበትን ሁሉ ነገረው። ከዚያም እርሱና ሳሙኤል ወደ ነዋት ሄደው ተቀመጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊት ሸሽቶ ካመለጠ በኋላ፥ ወደ ራማ ወደ ሳሙኤል ሄደ፥ ሳኦል ያደረገበትን ሁሉ ነገረው። ከዚያም እርሱና ሳሙኤል ወደ ናዮት ሄደው በዚያ ተቀመጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊትም አምልጦ ሳሙኤል ወደነበረበት ወደ ራማ መጣ፤ ሳኦል ያደረገበትንም በደል ሁሉ ነገረው፤ ከዚህም በኋላ ሳሙኤልና ዳዊት በራማ ወደምትገኘው ወደ ናዮት ሄደው በዚያ ተቀመጡ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም ሸሽቶ አመለጠ፥ ወደ አርማቴምም ወደ ሳሙኤል መጣ፥ ሳኦልም ያደረገበትን ሁሉ ነገረው፥ እርሱና ሳሙኤልም ሄዱ በነዋትዘራማም ተቀመጡ። |
ማልደውም ተነሥተው ለእግዚአብሔር ሰግደው ሄዱ፤ ወደ ቤታቸውም ወደ አርማቴም ደረሱ፤ ሕልቃናም ሚስቱን ሐናን ዐወቃት፤ እግዚአብሔርም አሰባት፤ ፀነሰችም።
ሳኦልም እጅግ ተቈጣ፤ እርሱም ደግሞ ወደ አርማቴም መጣ፤ በመሴፋም አውድማ ወዳለው ወደ ታላቁ የውኃ ጕድጓድ ደረሰ። “ሳሙኤልና ዳዊት የት ናቸው?” ብሎ ጠየቀ፤ “እነሆ፥ በአውቴዘራማ ናቸው” አሉት።
ወደ አውቴዘራማም ሄደ፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ በእርሱ ደግሞ ወረደ፤ እርሱም ሄደ፤ ወደ አውቴዘራማም እስኪመጣ ድረስ ትንቢት ይናገር ነበር።
ዳዊትም ከአውቴዘራማ ሸሸ፤ ወደ ዮናታንም መጣ፤ እንዲህም አለው፥ “ምን አደረግሁ? ምንስ በደልሁ? ነፍሴንም ይሻት ዘንድ በአባትህ ፊት ጥፋቴና ኀጢአቴ ምንድን ነው?”
የአንኩስ ብላቴኖችም፥ “ይህ ዳዊት የሀገሩ ንጉሥ አይደለምን? ሳኦል ሺህ፥ ዳዊትም ዐሥር ሺህ ገደለ ብለው ሴቶች በዘፈን የዘመሩለት እርሱ አይደለምን?” አሉት።
ሳሙኤል ግን ሞቶ ነበር፤ እስራኤልም ሁሉ አልቅሰውለት ነበር፤ በከተማውም በአርማቴም ቀብረውት ነበር። ሳኦልም መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችን ከምድር አጥፍቶ ነበር።
ቤቱም በዚያ ነበረና ወደ አርማቴም ይመለስ ነበር፤ በዚያም በእስራኤል ላይ ይፈርድ ነበር፤ በዚያም ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ።