1 ሳሙኤል 18:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳኦልም ዳዊትን፥ “ታላቂቱ ልጄ ሜሮብ እነኋት፤ እርስዋን እድርልሃለሁ፤ ብቻ ጀግና ልጅ ሁንልኝ፤ ስለ እግዚአብሔርም ጦርነት ተጋደል” አለው። ሳኦልም፥ “የፍልስጥኤማውያን እጅ በእርሱ ላይ ትሁን እንጂ የእኔ እጅ በእርሱ ላይ አትሁን” ይል ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳኦል ዳዊትን፣ “ታላቋ ልጄ ሜሮብ እነኋት፤ እርሷን እድርልሃለሁ፤ አንተ ግን በጀግንነት አገልግለኝ፤ የእግዚአብሔርንም ጦርነቶች ተዋጋ” አለው፤ ሳኦል በልቡ፣ “ፍልስጥኤማውያን እጃቸውን ያንሡበት እንጂ እኔ በርሱ ላይ እጄን አላነሣም” ብሎ ነበርና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳኦል ዳዊትን፥ “ታላቋ ልጄ ሜራብ እነኋት፤ እርሷን እድርልሃለሁ፤ አንተ ግን በጀግንነት አገልግለኝ፤ የጌታንም ጦርነቶች ተዋጋልኝ” አለው፤ ሳኦል በልቡ፥ “ፍልስጥኤማውያን እጃቸውን ያንሡበት እንጂ እኔ በእርሱ ላይ እጄን አላነሣም” ብሎ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ሳኦል ዳዊትን እንዲህ አለው፥ “የእግዚአብሔርን ጦርነት በጀግንነት ብትዋጋ ታላቅዋን ልጄን ሜራብን እድርልሃለሁ፤” ሳኦል ይህን ያለበት ምክንያት በፍልስጥኤማውያን እጅ እንዲሞት እንጂ እርሱ ዳዊትን ለመግደል ስላልፈለገ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳኦልም ዳዊትን፦ ታላቂቱ ልጄ ሜሮብ እነኋት፥ እርስዋን እድርልሃለሁ፥ ብቻ ቀልጣፋ ልጅ ሁንልኝ፥ ስለ እግዚአብሔርም ጦርነት ተጋደል አለው። ሳኦልም፦ የፍልስጥኤማውያን እጅ በእርሱ ላይ ትሁን እንጂ የእኔ እጅ በእርሱ ላይ አትሁን ይል ነበር። |
አሁንስ በፊቱ ክፉ ትሠራ ዘንድ የእግዚአብሔርን ነገር ለምን አቃለልህ? ኬጤያዊውን ኦርዮን በሰይፍ መትተሃል፤ ሚስቱንም ለአንተ ሚስት ትሆን ዘንድ ወስደሃል፤ እርሱንም በአሞን ልጆች ሰይፍ ገድለሃል።
የእግዚአብሔርም ታቦት ወደ ዳዊት ከተማ በደረሰች ጊዜ የሳኦል ልጅ ሜልኮል በመስኮት ሆና ተመለከተች፤ ንጉሡም ዳዊት በእግዚአብሔር ፊት ሲዘልልና ሲዘምር አየችው፥ በልብዋም ናቀችው።
እኛ አገልጋዮችህ ግን ሁላችን የጦር መሣሪያችንን ይዘን በእግዚአብሔር ፊት ጌታችን እንደ ተናገረ ወደ ጦርነት እንሄዳለን።”
ሙሴም፥ “የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች ሁላቸው የጦር መሣሪያቸውን ይዘው ከእናንተ ጋር በእግዚአብሔር ፊት ለጦርነት ዮርዳኖስን ቢሻገሩ፥ ምድሪቱንም ድል ብትነሡ ፥ የገለዓድን ምድር ርስት አድርጋችሁ ትሰጡአቸዋላችሁ።
እርሱን ለመግደል በመጀመሪያ የምስክሮች እጅ በኋላም የሕዝቡ ሁሉ እጅ ትሁንበት፤ እንዲሁ ክፉውን ከመካከላችሁ አስወግዱ።
የሳኦልም ወንዶች ልጆች ዮናታን፥ የሱዊ፥ ሚልኪሳ ነበሩ፤ የሁለቱም ሴቶች ልጆቹ ስም ይህ ነበረ፤ የታላቂቱ ስም ሜሮብ፥ የታናሺቱም ስም ሜልኮል ነበረ።
የእስራኤልም ሰዎች፥ “ይህን የወጣውን ሰው አያችሁትን? በእውነት እስራኤልን ሊገዳደር ወጣ፤ የሚገድለውንም ሰው ንጉሡ እጅግ ባለጠጋ ያደርገዋል፤ ልጁንም ይድርለታል፤ ያባቱንም ቤተ ሰብ በእስራኤል ዘንድ ከግብር ነጻ ያወጣቸዋል” አሉ።
እኔ ባሪያህ አንበሳና ድብ ገደልሁ፤ ይህም ያልተገረዘው ፍልስጥኤማዊ ከእነርሱ እንደ አንዱ ይሆናል። እንግዲህ እገድለው ዘንድ፥ ከእስራኤልም ተግዳሮትን አስወግድ ዘንድ ዛሬ አልሄድምን? የሕያው አምላክ ጭፍሮችን ይገዳደር ዘንድ ይህ ቈላፍ ምንድን ነው?”
ይህም ጉባኤ ሁሉ እግዚአብሔር በሰይፍና በጦር የሚያድን እንዳይደለ ያውቃል። ሰልፉ ለእግዚአብሔር ነውና፤ እግዚአብሔርም እናንተን በእጃችን አሳልፎ ይሰጣል።”
ሳኦልም፥ “እርስዋን እሰጠዋለሁ፤ እርስዋም እንቅፋት ትሆንበታለች” አለ። እነሆም፥ የፍልስጥኤማውያን እጅ በሳኦል ላይ ነበረች።
ሳኦልም አላቸው፥ “የንጉሥን ጠላቶች ይበቀል ዘንድ ከመቶ ፍልስጥኤማውያን ሸለፈት በቀር ንጉሥ ማጫ አይሻም ብላችሁ ለዳዊት ንገሩት” አላቸው። ሳኦል ግን ይህን ማለቱ በፍልስጥኤማውያን እጅ ይጥለው ዘንድ አስቦ ነው።
ዳዊትና ሰዎቹም ተነሥተው ሄዱ፤ ከፍልስጥኤማውያንም ሁለት መቶ ሰዎችን ገደሉ፤ ዳዊትም ለንጉሥ አማች ይሆን ዘንድ ሰለባቸውን አምጥቶ በቍጥራቸው ልክ ለንጉሡ ሰጠ። ሳኦልም ልጁን ሜልኮልን ዳረለት።
እግዚአብሔር ለጌታዬ የታመነ ቤትን ይሠራለታልና፥ የጌታዬንም ጦርነት እግዚአብሔር ይዋጋለታልና የእኔን የባሪያህን ኀጢኣት፥ እባክህ፥ ይቅር በል፤ በዘመንህም ሁሉ ክፋት አይገኝብህም።
ዳዊትም ወደ ሴቄላቅ በመጣ ጊዜ ለይሁዳ ሽማግሌዎችና ለወዳጆቹ፥ “እነሆ፥ ከእግዚአብሔር ጠላቶች ምርኮ በረከትን ተቀበሉ” ብሎ ከምርኮው ላከላቸው።