አስቀድሞ ሳኦል በእኛ ላይ ንጉሥ ሆኖ ሳለ እስራኤልን የምታወጣና የምታገባ አንተ ነበርህ፤ እግዚአብሔርም፦ አንተ ሕዝቤን እስራኤልን ትጠብቃለህ፤ በእስራኤልም ላይ አለቃ ትሆናለህ ብሎህ” ነበር።
1 ሳሙኤል 18:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህም ሳኦል ከእርሱ አራቀው፤ የሺህ አለቃም አድርጎ ሾመው፤ በሕዝቡም ፊት ይወጣና ይገባ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ዳዊትን ከአጠገቡ በማራቅ የሺሕ አለቃ አደረገው። ዳዊትም ሰራዊቱን እየመራ በፊታቸው ይወጣና ይገባ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ዳዊትን ከአጠገቡ በማራቅ የሺህ አለቃ አደረገው። ዳዊትም ሠራዊቱን እየመራ በፊታቸው ይወጣና ይገባ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም የተነሣ ሳኦል ዳዊትን ከፊቱ ለማራቅ የሺህ ወታደሮች አዛዥ አድርጎ ላከው፤ ዳዊትም ወታደሮቹን ወደ ጦርነት መራ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህም ሳኦል ከእርሱ አራቀው፥ የሺህ አለቃም አደረገው፥ በሕዝቡም ፊት ይወጣና ይገባ ነበር። |
አስቀድሞ ሳኦል በእኛ ላይ ንጉሥ ሆኖ ሳለ እስራኤልን የምታወጣና የምታገባ አንተ ነበርህ፤ እግዚአብሔርም፦ አንተ ሕዝቤን እስራኤልን ትጠብቃለህ፤ በእስራኤልም ላይ አለቃ ትሆናለህ ብሎህ” ነበር።
ሳኦልም አላቸው፥ “የንጉሥን ጠላቶች ይበቀል ዘንድ ከመቶ ፍልስጥኤማውያን ሸለፈት በቀር ንጉሥ ማጫ አይሻም ብላችሁ ለዳዊት ንገሩት” አላቸው። ሳኦል ግን ይህን ማለቱ በፍልስጥኤማውያን እጅ ይጥለው ዘንድ አስቦ ነው።
ሳኦልም በአጠገቡ የቆሙትን ብላቴኖች፥ “ብንያማውያን ሆይ! እንግዲህ ስሙ በእውነት የእሴይ ልጅ እርሻና የወይን ቦታ ለሁላችሁ ይሰጣችኋልን? ሁላችሁንስ መቶ አለቆችና ሻለቆች ያደርጋችኋልን?
ለራሱም የሻለቆችና የመቶ አለቆች የአምሳ አለቆችም ያደርጋቸዋል፤ እርሻውንም የሚያርሱ፥ እህሉንም የሚያጭዱ፥ ፍሬውንም የሚለቅሙ፥ የጦር መሣሪያውንና የሰረገሎቹንም ዕቃ የሚሠሩ ያደርጋቸዋል።