አሣሄልንም አንሥተው በቤተ ልሔም በአባቱ መቃብር ቀበሩት፤ ኢዮአብና ከእርሱ ጋር የነበሩ ሰዎቹም ሌሊቱን ሁሉ፤ ሄዱ፥ በኬብሮንም አነጉ።
1 ሳሙኤል 17:58 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳኦልም፥ “አንተ ብላቴና የማን ልጅ ነህ?” አለው ዳዊትም፥ “እኔ የቤተ ልሔሙ የባሪያህ የእሴይ ልጅ ነኝ” ብሎ መለሰ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳኦልም፣ “አንተ ወጣት፣ የማን ልጅ ነህ?” ሲል ጠየቀው። ዳዊትም፣ “እኔ የአገልጋይህ የቤተ ልሔሙ ሰው የእሴይ ልጅ ነኝ” ሲል መለሰ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳኦልም “አንተ ወጣት የማን ልጅ ነህ?” ብሎ ጠየቀው። ዳዊትም “የቤተልሔም ነዋሪ የሆነው የአገልጋይህ የእሴይ ልጅ ነኝ” ሲል መለሰለት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳኦልም “አንተ ወጣት የማን ልጅ ነህ?” ብሎ ጠየቀው። ዳዊትም “የቤተልሔም ነዋሪ የሆነው የአገልጋይህ የእሴይ ልጅ ነኝ” ሲል መለሰለት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳኦልም፦ አንተ ብላቴና፥ የማን ልጅ ነህ? አለው። ዳዊትም፦ እኔ የቤተ ልሔሙ የባሪያህ የእሴይ ልጅ ነኝ ብሎ መለሰ። |
አሣሄልንም አንሥተው በቤተ ልሔም በአባቱ መቃብር ቀበሩት፤ ኢዮአብና ከእርሱ ጋር የነበሩ ሰዎቹም ሌሊቱን ሁሉ፤ ሄዱ፥ በኬብሮንም አነጉ።
እግዚአብሔርም ሳሙኤልን፥ “በእስራኤል ላይ እንዳይነግሥ ለናቅሁት ለሳኦል የምታለቅስለት እስከ መቼ ነው? የዘይቱን ቀንድ ሞልተህ ና፤ በልጆቹ መካከል ለእኔ ንጉሥ አዘጋጅቼአለሁና ወደ እሴይ ወደ ቤተ ልሔም እልክሃለሁ” አለው።
ዳዊትም የዚያ የኤፍራታዊው ሰው ልጅ ነበረ፤ ያም ሰው ከቤተ ልሔም ይሁዳ ስሙም እሴይ ነበረ፤ ስምንት ልጆችም ነበሩት፤ እሴይም በሳኦል ዘመን በዕድሜ አርጅቶ ሸምግሎም ነበር።
አባትህም ቢፈልገኝ፦ ለዘመዶቹ ሁሉ በዚያ በቤተ ልሔም የዓመት መሥዋዕት አላቸውና ዳዊት ወደ ከተማው ፈጥኖ ይሄድ ዘንድ አጽንቶ ለምኖኛል በለው።