1 ሳሙኤል 16:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እሴይም ሣማዕን አሳለፈው፤ እርሱም፥ “ይህን ደግሞ እግዚአብሔር አልመረጠውም” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እሴይም ሣማን አሳለፈ፤ ሳሙኤልም፣ “እርሱንም እግዚአብሔር አልመረጠውም” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እሴይም ሻማን አሳለፈ፤ ሳሙኤልም፥ “እርሱንም ጌታ አልመረጠውም” አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀጥሎም እሴይ ሻማ ተብሎ የሚጠራውን ልጁን አመጣ፤ ሳሙኤል ግን “እግዚአብሔር ይህኛውንም አልመረጠም” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እሴይም ሣማን አሳለፈው፥ እርሱም፦ ይህን ደግሞ እግዚአብሔር አልመረጠውም አለ። |
እሴይም ከልጆቹ ሰባቱን በሳሙኤል ፊት አሳለፋቸው። ሳሙኤልም እሴይን፥ “እግዚአብሔር እነዚህን አልመረጠም” አለው።
የእሴይም ሦስቱ ታላላቆች ልጆቹ ሳኦልን ተከትለው ወደ ሰልፉ ሄደው ነበር፤ ወደ ሰልፉም የሄዱት የሦስቱ ልጆች ስም ይህ ነበረ፤ ታላቁ ኤልያብ፥ ሁለተኛውም አሚናዳብ፥ ሦስተኛውም ሣማዕ ነበረ።