La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ሳሙኤል 16:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሳሙ​ኤ​ልም እሴ​ይን፥ “ልጆ​ችህ እኒህ ብቻ ናቸው?” አለው። እር​ሱም፥ “ታናሹ ገና ቀር​ቶ​አል፤ እነ​ሆም፥ በጎ​ችን ይጠ​ብ​ቃል” አለ። ሳሙ​ኤ​ልም እሴ​ይን፥ “እርሱ እስ​ኪ​መጣ ድረስ ለማ​ዕድ አን​ቀ​መ​ጥ​ምና ልከህ አስ​መ​ጣው” አለው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ቀጥሎም እሴይን፣ “ልጆችህ እነዚሁ ብቻ ናቸውን?” ሲል ጠየቀው። እሴይም፣ “የሁሉም ታናሽ ገና አልመጣም፤ ነገር ግን በጎች እየጠበቀ ነው” ብሎ መለሰ። ሳሙኤልም፣ “በል ልከህ አስመጣው፤ እስኪመጣ ድረስ አንቀመጥምና” አለው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ቀጥሎም እሴይን፥ “ልጆችህ እነዚሁ ብቻ ናቸውን?” ሲል ጠየቀው። እሴይም፥ “የሁሉም ታናሽ ገና አልመጣም፤ ነገር ግን በጎች እየጠበቀ ነው” ብሎ መለሰ። ሳሙኤልም እሴይን፥ “በል ልከህ አስመጣው፤ እስኪመጣ ድረስ አንቀመጥም” አለው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“ታዲያ ሌሎች ልጆች የሉህምን?” ሲል ጠየቀው። እሴይም “የሁሉ ታናሽ የሆነ አንድ ልጅ አለ፤ እርሱ ግን ወደ በግ እረኝነት ሄዶአል” ሲል መለሰለት። ሳሙኤልም “እርሱን አስጠርተህ አምጣው፤ እርሱ ሳይመጣ መሥዋዕት አናቀርብም” አለው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሳሙኤልም እሴይን፦ የቀረ ሌላ ልጅ አለህን? አለው። እርሱም፦ ታናሹ ገና ቀርቶአል፥ እነሆም፥ በጎችን ይጠብቃል አለ። ሳሙኤልም እሴይን፦ እርሱ እስኪመጣ ድረስ አንረፍቅምና ልከህ አስመጣው አለው።

Ver Capítulo



1 ሳሙኤል 16:11
8 Referencias Cruzadas  

ለአ​ም​ኖ​ንም የዳ​ዊት ወን​ድም የሳ​ምዓ ልጅ ኢዮ​ና​ዳብ የሚ​ባል ወዳጅ ነበ​ረው፤ ኢዮ​ና​ዳ​ብም እጅግ ብልህ ሰው ነበረ።


አሁ​ንም ዳዊ​ትን ባሪ​ያ​ዬን እን​ዲህ በለው፦ ሁሉን የሚ​ገዛ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በሕ​ዝቤ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ አለቃ ትሆን ዘንድ ከበግ ጥበቃ ወሰ​ድ​ሁህ፤


አሁ​ንም አገ​ል​ጋ​ዬን ዳዊ​ትን እን​ዲህ በለው፦ ሁሉን ቻይ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ አንተ መን​ጋ​ውን ስት​ከ​ተል በሕ​ዝቤ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ አለቃ ትሆን ዘንድ ከበግ ጥበቃ መርጬ ወሰ​ድ​ሁህ።


ሙሴም የአ​ማ​ቱን የም​ድ​ያ​ምን ካህን የዮ​ቶ​ርን በጎች ይጠ​ብቅ ነበር፤ በጎ​ቹ​ንም ወደ ምድረ በዳ ዳርቻ ነዳ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ተራራ ወደ ኮሬብ መጣ።


እሴ​ይም ከል​ጆቹ ሰባ​ቱን በሳ​ሙ​ኤል ፊት አሳ​ለ​ፋ​ቸው። ሳሙ​ኤ​ልም እሴ​ይን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እነ​ዚ​ህን አል​መ​ረ​ጠም” አለው።


ታላቅ ወን​ድ​ሙም ኤል​ያብ ከሰ​ዎች ጋር ሲነ​ጋ​ገር ሰማ፤ ኤል​ያ​ብም በዳ​ዊት ላይ እጅግ ተቈጣ፥ “ለምን ወደ​ዚህ ወረ​ድህ? እነ​ዚ​ያ​ንስ ጥቂ​ቶች በጎች በም​ድረ በዳ ለማን ተው​ሃ​ቸው? እኔ ኵራ​ት​ህ​ንና የል​ብ​ህን ክፋት አው​ቃ​ለ​ሁና ሰል​ፉን ለማ​የት መጥ​ተ​ሃል” አለው።