1 ሳሙኤል 15:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳኦልም አማሌቃውያንን ከኤውላጥ ጀምሮ በግብፅ ፊት እስካለችው እስከ ሱር ድረስ መታቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ሳኦል አማሌቃውያንን ከኤውላጥ አንሥቶ በምሥራቅ ግብጽ እስካለው እስከ ሱር ድረስ ወጋቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ሳኦል አማሌቃውያንን ከኤውላጥ አንሥቶ በምሥራቅ ግብጽ እስካለው እስከ ሱር ድረስ ወጋቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳኦል ከሐዊላ ጀምሮ በግብጽ ምሥራቅ እስከምትገኘው እስከ ሹር በሚያደርሰው መንገድ ሁሉ ዐማሌቃውያንን ድል አደረገ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳኦልም አማሌቃውያንን ከኤውላጥ ጀምሮ በግብጽ ፊት እስካለችው እስከ ሱር ድረስ መታቸው። |
ሙሴም የእስራኤልን ልጆች ከኤርትራ ባሕር አውጥቶ ወደ ሱር ምድረ በዳ ወሰዳቸው። በምድረ በዳም ሦስት ቀን ተጓዙ፤ ይጠጡም ዘንድ ውኃ አላገኙም።
ዳዊትና ሰዎቹም ወጥተው በጌሴራውያንና በአማሌቃውያን ላይ አደጋ ጣሉ፤ እነዚህንም ቅጽር ባላቸው በጌላምሱርና በአኔቆንጦን እስከ ግብፅ ምድር ድረስ ተቀምጠው አገኙአቸው።
እንዲህም ሆነ፤ ዳዊትና ሰዎቹ በሦስተኛው ቀን ወደ ሴቄላቅ በገቡ ጊዜ፥ አማሌቃውያን በአዜብ በሰቄላቅም ላይ ዘምተው ነበር፤ ሴቄላቅንም መትተው በእሳት አቃጥለዋት ነበር፥