1 ሳሙኤል 13:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከፍልስጥኤማውያንም ሰፈር ማራኪዎች በሦስት ክፍል ሆነው ወጡ፤ አንዱም ክፍል በጎፌር መንገድ ወደ ሦጋክ ምድር ሄደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሦስት ምድብ የተከፈሉ ወራሪዎች ከፍልስጥኤማውያን ሰፈር ወጡ፤ አንዱ ምድብ በሦጋል ግዛት ወደሚገኘው ወደ ዖፍራ አቀና፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሦስት ምድብ የተከፈሉ ወራሪዎች ከፍልስጥኤማውያን ሰፈር ወጡ፤ አንዱ ምድብ በሹዓል ግዛት ወደሚገኘው ወደ ዖፍራ አቅጣጫ አመራ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የፍልስጥኤማውያን ወታደሮች በሦስት ክፍል ተከፍለው ወረራ ለማድረግ ከምሽጋቸው ወጡ፤ አንዱ ቡድን በሹዓል ግዛት ወደሚገኘው ወደ ዖፍራ አቅጣጫ አመራ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከፍልስጥኤማውያንም ሰፈር ማራኪዎች በሦስት ክፍል ሆነው ወጡ፥ አንዱም ክፍል በዖፍራ መንገድ ወደ ሦጋል ምድር ሄደ። |
በነጋውም ሳኦል ሕዝቡን በሦስት ወገን አደረጋቸው፤ወገግም ባለ ጊዜ ወደ ሰፈሩ መካከል ገቡ፤ ቀትርም እስኪሆን ድረስ አሞናውያንን መቱ፤ የቀሩትም ተበተኑ፤ ከውስጣቸውም ሁለት በአንድ ላይ ሆነው አልተገኙም።
በሰፈሩና በእርሻውም ድንጋጤ ሆነ፤ በሰፈሩ የተቀመጡ ሕዝብና የሚዋጉትም ሁሉ ተሸበሩ፤ መዋጋትም አልቻሉም፤ ምድሪቱም ተናወጠች፤ ከእግዚአብሔርም ዘንድ ታላቅ ድንጋጤ መጣ።