1 ሳሙኤል 12:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳሙኤልም ለእስራኤል ሕዝብ ሁሉ አለ፥ “የነገራችሁኝን ሁሉ ሰምቼ ንጉሥ አንግሼላችኋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳሙኤል ለመላው እስራኤል እንዲህ አለ፤ “እነሆ፤ ያላችሁኝን ሁሉ ሰምቼ ንጉሥ አንግሼላችኋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳሙኤል ለመላው እስራኤል እንዲህ አለ፤ “እነሆ፤ ያላችሁኝን ሁሉ ሰምቼ ንጉሥ አንግሼላችኋለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ሳሙኤል ለእስራኤል ሕዝብ እንዲህ አለ፤ “ጥያቄአችሁን ሁሉ ተቀብዬ ንጉሥ አንግሼላችኋለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳሙኤልም እስራኤልን ሁሉ አለ፦ የነገራችሁኝን ሁሉ ሰምቼ አንግሼላችኋለሁ። |
ሳሙኤልም የዘይቱን ቀንድ ወስዶ በራሱ ላይ አፈሰሰው፤ ሳመውም፤ እንዲህም አለው፥ “በሕዝቡ በእስራኤል ላይ ትነግሥ ዘንድ እግዚአብሔር ቀብቶሃል፤ የእግዚአብሔርንም ሕዝብ ትገዛለህ፤ በዙሪያውም ካሉ ጠላቶቻቸው እጅ ታድናቸዋለህ። እግዚአብሔርም በርስቱ ላይ ትነግሥ ዘንድ እንደ ቀባህ ምልክቱ ይህ ነው።
ሳሙኤልም ለሕዝቡ ሁሉ፥ “ከሕዝቡ ሁሉ እርሱን የሚመስል እንደ ሌለ እግዚአብሔር የመረጠውን ታያላችሁን?” አላቸው፤ ሕዝቡም ሁሉ፥ “ንጉሥ ሕያው ይሁን” እያሉ እልልታ አደረጉ።
አሁንም ቃላቸውን ስማ፤ ነገር ግን ጽኑ ምስክር መስክርባቸው፤ በእነርሱም ላይ የሚነግሠውን የንጉሡን ሥርዐት ንገራቸው።”