La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ሳሙኤል 11:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እነ​ሆም፥ ሳኦል ከእ​ር​ሻው አር​ፍዶ መጣ፤ ሳኦ​ልም፥ “ሕዝቡ የሚ​ያ​ለ​ቅስ ምን ሆኖ ነው?” አለ። የኢ​ያ​ቢ​ስ​ንም ሰዎች ነገር ነገ​ሩት።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በዚህ ጊዜ፣ ሳኦል በሬዎቹን እየነዳ ከዕርሻ ተመለሰ፤ እርሱም፣ “ሕዝቡ የሚያለቅሰው ምን ሆኖ ነው?” ሲል ጠየቀ። እነርሱም የኢያቢስ ሰዎች ያሏቸውን ነገሩት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በዚህ ጊዜ ሳኦል በሬዎቹን እየነዳ ከእርሻ ተመለሰ፤ እርሱም፥ “ሕዝቡ የሚያለቅሰው ምን ሆኖ ነው?” ሲል ጠየቀ። እነርሱም የያቢሽ ሰዎች ያሏቸውን ነገሩት።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሳኦል በዚህ ጊዜ ጥንድ በሬዎቹን ይዞ ከዋለበት እርሻ በመመለስ ላይ ነበር፤ እርሱም “ምንድን ነው ነገሩ? ሰው ሁሉ የሚያለቅሰው ስለምንድን ነው?” ሲል ጠየቀ፤ እነርሱም ከያቤሽ የመጡ መልእክተኞች የሚሉትን ወሬ ነገሩት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እነሆም፥ ሳኦል በሬዎቹን ተከትሎ ከእርሻው መጣ፥ ሳኦልም፦ ሕዝቡ የሚያለቅስ ምን ሆኖ ነው? አለ። የኢያቢስንም ሰዎች ነገር ነገሩት።

Ver Capítulo



1 ሳሙኤል 11:5
6 Referencias Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሕ​ፃ​ኑን ጩኸት ሰማ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ከሰ​ማይ አጋ​ርን እን​ዲህ ሲል ጠራት፥ “አጋር ሆይ፥ ምን ሆንሽ? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የል​ጅ​ሽን ድምፅ ባለ​በት ስፍራ ሰም​ቶ​አ​ልና አት​ፍሪ።


ከዚ​ያም ሄደ፤ የሣ​ፋ​ጥ​ንም ልጅ ኤል​ሳ​ዕን በዐ​ሥራ ሁለት ጥማድ በሬ​ዎች ሲያ​ርስ፥ እር​ሱም ከዐ​ሥራ ሁለ​ተ​ኛው ጋር ሆኖ አገ​ኘው። ኤል​ያ​ስም ወደ እርሱ አልፎ መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያ​ውን ጣለ​በት።


ስለ ጽዮን ሸለቆ የተ​ነ​ገረ ቃል። እና​ንተ ሁላ​ችሁ፥ ዛሬ ወደ ሰገ​ነት በከ​ንቱ መው​ጣ​ታ​ችሁ ምን ሆና​ች​ኋል?


ወደ ዳንም ልጆች ጮኹ፤ የዳ​ንም ልጆች ፊታ​ቸ​ውን መል​ሰው ሚካን፥ “የም​ት​ጮ​ኸው ምን ሆነህ ነው?” አሉት።


ከብ​ን​ያም ልጆች ስሙ ቂስ የተ​ባለ አንድ ሰው ነበረ፥ እር​ሱም የአ​ብ​ሔል ልጅ፥ የያ​ሬድ ልጅ፥ የባ​ሔር ልጅ፥ የብ​ን​ያም ሰው፥ የአ​ፌቅ ልጅ፥ ጽኑዕ ኀያል ሰው ነበረ።