ዳዊትም፥ “እናንተ የሶርህያ ልጆች! ዛሬ ታስቱኝ ዘንድ በእኔና በእናንተ መካከል ምን አለኝ? ዛሬስ ከእስራኤል የሚሞት አንድ ሰው የለም። ዛሬስ በእስራኤል ላይ እንደ ነገሥሁ አላውቅምን?”
1 ሳሙኤል 11:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳኦልም፦“በዚያች ቀን እግዚአብሔር ለእስራኤል ድኅነትን አድርጎአልና ዛሬ አንድ ሰው አይሞትም” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳኦል ግን፣ “ይህ ዕለት እግዚአብሔር እስራኤልን የታደገበት ቀን ስለ ሆነ፣ በዛሬው ዕለት ማንም ሰው አይገደልም” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳኦል ግን፥ “ይህ ዕለት ጌታ እስራኤልን የታደገበት ቀን ሰለሆነ፥ በዛሬው ዕለት ማንም ሰው አይገደልም” አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳኦል ግን “በዛሬው ቀን እግዚአብሔር እስራኤልን ስላዳነ ማንም ሰው መገደል የለበትም” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳኦልም፦ ዛሬ እግዚአብሔር ለእስራኤል ማዳን አድርጎአልና ዛሬ አንድ ሰው አይሞትም አለ። |
ዳዊትም፥ “እናንተ የሶርህያ ልጆች! ዛሬ ታስቱኝ ዘንድ በእኔና በእናንተ መካከል ምን አለኝ? ዛሬስ ከእስራኤል የሚሞት አንድ ሰው የለም። ዛሬስ በእስራኤል ላይ እንደ ነገሥሁ አላውቅምን?”
የእስራኤልም ሰዎች በጮኹ ጊዜ እርሱ ተነሥቶ እጁ እስከሚደክምና ከሰይፉ ጋር እስኪጣበቅ ድረስ ፍልስጥኤማውያንን መታ፤ በዚያም ቀን እግዚአብሔር ታላቅ መድኀኒት አደረገ፤ ሕዝቡም ከእርሱ በኋላ የሞቱትን ለመግፈፍ ብቻ ተመለሱ።
ሙሴም ለሕዝቡ፥ “አትፍሩ፤ ዛሬ የምታዩአቸውን ግብፃውያንን ለዘለዓለም አታዩአቸውምና ቁሙ፤ ዛሬ ለእናንተ የሚያደርጋትን የእግዚአብሔርን ማዳን እዩ።
እግዚአብሔርም በዚያ ቀን እስራኤልን ከግብፃውያን እጅ አዳናቸው፤ እስራኤልም ግብፃውያን እንደ ሞቱ በባሕር ዳር አዩ።
ነገር ግን በእግዚአብሔር ጸጋ አሁን እኔ ባለሁበት አለሁ፤ ለእኔም የሰጠኝ ጸጋው ለከንቱ የሆነብኝ አይደለም፤ እኔም ከሁሉ ይልቅ ደከምሁ፤ ነገር ግን በእኔ ላይ ያደረው የእግዚአብሔር ጸጋ አጸናኝ እንጂ እኔ አይደለሁም።
ሕዝቡም ሳኦልን፥ “በውኑ በእስራኤል ዘንድ ታላቅ መድኀኒት ያደረገ ዮናታን ዛሬ ይሞታልን? ይህ አይሁን፤ ዛሬ ለሕዝቡ ከእግዚአብሔር ጋር አድርጎአልና ሕያው እግዚአብሔርን! ከራሱ ጠጕር አንዲት በምድር ላይ አትወድቅም” አሉት። ሕዝቡም ያን ጊዜ ስለ ዮናታን ጸለዩ፤ እርሱም አልተገደለም።
ነፍሱንም በእጁ ጥሎ ፍልስጥኤማዊዉን ገደለ፤ እግዚአብሔርም በእርሱ ታላቅ መድኀኒት አደረገ፤ እስራኤልም ሁሉ አይተው ደስ አላቸው፤ በከንቱ ዳዊትን ትገድለው ዘንድ ስለምን በንጹሕ ደም ላይ ትበድላለህ?”