La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ሳሙኤል 10:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ዛሬ ከእኔ በተ​ለ​የህ ጊዜ በብ​ን​ያም ግዛት በቤ​ቴል አው​ራጃ በራ​ሔል መቃ​ብር አጠ​ገብ ሁለት ሰዎች እየ​ቸ​ኰሉ ሲሄዱ ታገ​ኛ​ለህ፤ እነ​ር​ሱም፦ ልት​ፈ​ል​ጉ​አ​ቸው ሂዳ​ችሁ የነ​በ​ራ​ች​ሁ​ላ​ቸው አህ​ዮች ተገ​ኝ​ተ​ዋል፤ እነ​ሆም፥ አባ​ትህ ስለ አህ​ዮቹ ማሰብ ትቶ፦ የል​ጄን ነገር እን​ዴት አደ​ር​ጋ​ለሁ? እያለ ስለ እና​ንተ ይጨ​ነ​ቃል ይሉ​ሃል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ዛሬ ከእኔ ተለይተህ ስትሄድ፣ በብንያም ወሰን ላይ በምትገኘው ጼልጻህ በተባለች ስፍራ በራሔል መቃብር አጠገብ ሁለት ሰዎች ታገኛለህ። እነርሱም፣ ‘የምትፈልጋቸው አህዮች ተገኝተዋል፤ አሁን አባትህ ስለ አህዮቹ ማሰቡን ትቶ፣ “ስለ ልጄ ምን ባደርግ ይሻለኛል?” እያለ በመጨነቅ ላይ ነው’ ይሉሃል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ዛሬ ከእኔ ተለይተህ ስትሄድ፥ በብንያም ወሰን ላይ በምትገኘው ጼልጻህ በተባለች ስፍራ በራሔል መቃብር አጠገብ ሁለት ሰዎች ታገኛለህ። እነርሱም፥ ‘የምትፈልጋቸው አህዮች ተገኝተዋል፤ አሁን አባትህ ስለ አህዮቹ ማሰቡን ትቶ፥ ስለ ልጄ ምን ባደርግ ይሻለኛል?’ እያለ በመጨነቅ ላይ ነው” ይሉሃል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ዛሬ ከእኔ ተለይተህ በምትሄድበት ጊዜ፥ በብንያም ግዛት በሚገኘው ጼልጻሕ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ባለው በራሔል መቃብር አጠገብ ሁለት ሰዎች ታገኛለህ፤ እነርሱም ስትፈልጋቸው የነበሩ አህዮች መገኘታቸውንና አባትህም ስለ እነርሱ ማሰቡን ትቶ ስለ አንተ በመጨነቅ ‘እንግዲህ ስለ ልጄ ምን ላድርግ’ እያለ በመጠየቅ ላይ መሆኑን ይነግሩሃል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ዛሬ ከእኔ በተለየህ ጊዜ በብንያም ዳርቻ በጼልጻህ አገር ባለው በራሔል መቃብር አጠገብ ሁለት ሰዎች ታገኛለህ፥ እነርሱም፦ ልትሻቸው ሄደህ የነበርህላቸው አህዮች ተገኝተዋል፥ እነሆም፥ አባትህ ስለ አህዮች ማሰብ ትቶ፥ የልጄን ነገር እንዴት አደርጋለሁ? እያለ ስለ እናንተ ይጨነቃል ይሉሃል።

Ver Capítulo



1 ሳሙኤል 10:2
7 Referencias Cruzadas  

ያዕ​ቆ​ብም ከቤ​ቴል ተጓዘ፤ በጋ​ዲር ግንብ አጠ​ገብ ድን​ኳን ተከለ፤ ወደ ኤፍ​ራ​ታም ለመ​ድ​ረስ በቀ​ረበ ጊዜ ራሔ​ልን ምጥ ያዛት፤ በም​ጡም ተጨ​ነ​ቀች።


እኔም ከሶ​ርያ መስ​ጴ​ጦ​ምያ በመ​ጣሁ ጊዜ፥ ወደ ኤፍ​ራታ ለመ​ግ​ባት ጥቂት ቀር​ቶኝ በፈ​ረስ መጋ​ለ​ቢ​ያው መን​ገድ ሳለሁ፥ ራሔል በከ​ነ​ዓን ምድር ሞተ​ች​ብኝ፤ በዚ​ያም በኤ​ፍ​ራታ ወደ ፈረስ መጋ​ለ​ቢያ በሚ​ወ​ስ​ደው መን​ገድ ላይ ቀበ​ር​ኋት፤ እር​ስ​ዋም ቤተ ልሔም ናት።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “የኀ​ዘን፥ የል​ቅ​ሶና የጩ​ኸት ድምፅ በራማ ተሰማ፤ ራሔል ስለ ልጆ​ችዋ አለ​ቀ​ሰች፤ የሉ​ምና ስለ ልጆ​ችዋ መጽ​ና​ና​ትን እንቢ አለች።


ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም የም​ት​ባል የኢ​ያ​ቡ​ሴ​ዎን ከተ​ማና የኢ​ያ​ሪ​ሞን ከተማ ገባ​ዖን፤ ዐሥራ ሦስት ከተ​ሞ​ችና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው። የብ​ን​ያም ልጆች ርስት በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው ይህ ነበረ።


ሳኦ​ልም ለቤተ ሰቡ፥ “አህ​ዮች እንደ ተገኙ ገለ​ጠ​ልን” አለው፤ ነገር ግን የመ​ን​ግ​ሥ​ትን ነገር አላ​ወ​ራ​ለ​ትም።