La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ሳሙኤል 10:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሳኦ​ልም ለቤተ ሰቡ፥ “አህ​ዮች እንደ ተገኙ ገለ​ጠ​ልን” አለው፤ ነገር ግን የመ​ን​ግ​ሥ​ትን ነገር አላ​ወ​ራ​ለ​ትም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሳኦልም መልሶ፣ “አህዮቹ መገኘታቸውን ገልጾ ነገረን” አለው። ይሁን እንጂ ስለ መንገሡ ሳሙኤል የነገረውን ለአጎቱ አልተናገረም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሳኦልም መልሶ፥ “አህዮቹ መገኘታቸውን ገልጦ ነገረን” አለው። ነገር ግን ስለ መንገሡ ሳሙኤል የነገረውን ለአጎቱ አልተናገረም።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሳኦልም “የአህዮቹን መገኘት ነግሮናል” ሲል መለሰለት፤ ነገር ግን ንጉሥ ስለ መሆኑ ሳሙኤል የነገረውን ሁሉ ለአጐቱ አላወራለትም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሳኦልም አጎቱን፦ አህዮች እንደ ተገኙ ገለጠልን አለው፥ ነገር ግን ሳሙኤልን የነገረውን የመንግሥትን ነገር አላወራለትም።

Ver Capítulo



1 ሳሙኤል 10:16
9 Referencias Cruzadas  

ሙሴም ሄደ፤ ወደ አማቱ ወደ ዮቶ​ርም ተመ​ለሰ፥ “እስከ ዛሬ በሕ​ይ​ወት እንደ አሉ አይ ዘንድ ተመ​ልሼ ወደ ግብፅ ወደ ወን​ድ​ሞች እሄ​ዳ​ለሁ” አለው። ዮቶ​ርም ሙሴን፥ “በደ​ኅና ሂድ” አለው።


ብልህ ሰው የጥበብ መንበር ነው፤ የሰነፎች ልብ ግን መርገምን ያገኛል።


ለመ​ቅ​ደድ ጊዜ አለው፥ ለመ​ስ​ፋ​ትም ጊዜ አለው፤ ዝም ለማ​ለት ጊዜ አለው፥ ለመ​ና​ገ​ርም ጊዜ አለው፤


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ በእ​ርሱ ላይ አደረ፤ የፍ​የል ጠቦ​ትን እን​ደ​ሚ​ጥ​ልም ጣለው፤ በእ​ጁም እንደ ኢም​ንት ሆነ፤ ያደ​ረ​ገ​ው​ንም ለአ​ባ​ቱና ለእ​ናቱ አል​ተ​ና​ገ​ረም።


ወስ​ዶም በላ፤ እየ​በ​ላም ሄደ፤ ወደ አባ​ቱና ወደ እና​ቱም ደረሰ፤ ሰጣ​ቸ​ውም፤ እነ​ር​ሱም በሉ፤ ማሩ​ንም ከአ​ን​በ​ሳው አፍ ውስጥ እን​ዳ​ወ​ጣው አል​ነ​ገ​ራ​ቸ​ውም።


ያም ቤተ ሰብ፥ “ሳሙ​ኤል ምን አለ? እባ​ክህ! ንገ​ረኝ” አለው፤


ከሦ​ስት ቀንም በፊት የጠፉ አህ​ዮ​ችህ ተገ​ኝ​ተ​ዋ​ልና ልብ​ህን አታ​ስ​ጨ​ን​ቀው። የእ​ስ​ራ​ኤል መል​ካም ምኞት ለማን ነው? ለአ​ን​ተና ለአ​ባ​ትህ ቤት አይ​ደ​ለ​ምን?” አለው።


እነ​ር​ሱም በከ​ተ​ማ​ዪቱ ዳር ሲወ​ርዱ ሳሙ​ኤል ሳኦ​ልን፥ “ብላ​ቴ​ናው ወደ ፊታ​ችን እን​ዲ​ያ​ልፍ እዘ​ዘው፤ አንተ ግን ከእኔ ጋር ከዚህ ቁምና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስማ” አለው። ብላ​ቴ​ና​ውም አለፈ።