አዛሄልም፥ “ጌታዬን ምን ያስለቅሰዋል?” አለ። ኤልሳዕም፥ “በእስራኤል ልጆች ላይ የምታደርገውን ክፋት ስለማውቅ ነው፤ ምሽጎቻቸውን በእሳት ታቃጥላለህ፤ ጐልማሶቻቸውንም በሰይፍ ትገድላለህ፤ ሕፃናቶቻቸውንም ትፈጠፍጣለህ፤ እርጉዞቻቸውንም ትሰነጥቃለህ፤” አለው።
1 ሳሙኤል 1:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባልዋ ሕልቃናም፥ “ሐና ሆይ!” አላት እርስዋም፥ “ጌታዬ እነሆኝ” አለችው። እርሱም፥ “ለምን ታለቅሻለሽ? ለምንስ አትበዪም? ለምንስ ልብሽ ያዝንብሻል? እኔስ ከዐሥር ልጆች አልሻልሽምን?” አላት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ባሏ ሕልቃናም እርሷን፣ “ሐና ሆይ፤ ለምን ታለቅሻለሽ? ለምንስ አትበዪም? ልብሽስ ለምን ያዝናል? ከዐሥር ወንዶች ልጆች እኔ አልበልጥብሽምን?” ይላት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባሏ ሕልቃናም እርሷን፥ “ሐና ሆይ፥ ለምን ታለቅሻለሽ? ለምንስ አትበዪም? ልብሽስ ለምን ያዝናል? ከዐሥር ወንዶች ልጆች እኔ አልበልጥብሽምን?” ይላት ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም የተነሣ ባልዋ ሕልቃና “ሐና ሆይ! ስለምን ታለቅሻለሽ? ስለምንስ አትመገቢም? ስለምንስ ዘወትር ይህን ያኽል ታዝኚአለሽ? ከዐሥር ልጆች ይልቅ እኔ አልበልጥብሽምን?” ይላት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባልዋም ሕልቃና፦ ሐና ሆይ፥ ለምን ታለቅሻለሽ? ለምንስ አትቀምሺም? ለምንስ ልብሽ ያዝንብሻል? እኔስ ከአሥር ልጆች አልሻልልሽምን? አላት። |
አዛሄልም፥ “ጌታዬን ምን ያስለቅሰዋል?” አለ። ኤልሳዕም፥ “በእስራኤል ልጆች ላይ የምታደርገውን ክፋት ስለማውቅ ነው፤ ምሽጎቻቸውን በእሳት ታቃጥላለህ፤ ጐልማሶቻቸውንም በሰይፍ ትገድላለህ፤ ሕፃናቶቻቸውንም ትፈጠፍጣለህ፤ እርጉዞቻቸውንም ትሰነጥቃለህ፤” አለው።
አንቺ ያልወለድሽ መካን ሆይ፥ ደስ ይበልሽ፤ አንቺ ያላማጥሽ ሆይ፥ እልል በዪ፤ ጩኺም፤ ባል ካላት ይልቅ ፈት የሆነቺቱ ልጆች በዝተዋልና፥ ይላል እግዚአብሔር።
እግዚአብሔር እንደ ተተወችና እንደ ተበሳጨች፥ በልጅነቷም እንደ ተጠላች ሴት የጠራሽ አይደለም፥ ይላል አምላክሽ።
እነዚያ መላእክትም፥ “አንቺ ሴት፥ ምን ያስለቅስሻል?” አሉአት፤ እርስዋም፥ “ጌታዬን ከመቃብር ውስጥ ወስደውታል፤ ወዴትም እንደ ወሰዱት አላውቅም” አለቻቸው።
ጌታችን ኢየሱስም፥ “አንቺ ሴት፥ ምን ያስለቅስሻል? ማንንስ ትሺያለሽ?” አላት፤ እርስዋ ግን የአትክልት ቦታ ጠባቂ መስሎአት፥ “ጌታዬ፥ አንተ ወስደኸው እንደ ሆነ ሄጄ ወደ እኔ እንዳመጣውና ሽቱ እንድቀባው ወዴት እንደ አኖርኸው ንገረኝ” አለችው።
ወንድሞች ሆይ! እንመክራችኋለን፤ ያለ ሥርዐት የሚሄዱትን ገሥጹአቸው፤ ድፍረት የሌላቸውን አጽኑአቸው፤ ለደካሞች ትጉላቸው፤ ሰውን ሁሉ ታገሡ።
በየዓመቱም ወደ እግዚአብሔር ቤት በሚወጣበት ጊዜ እንዲህ ያደርግ ነበር፤ እርስዋም ትበሳጭና ታለቅስ ነበር። እህልም አትበላም ነበር።