አቤቱ ሁሉን የምትገዛ የእስራኤል አምላክ ሆይ፥ አሁንም ለባሪያህና ለቤቱ የተናገርኸውን ለዘለዓለም አጽናው፤ አሁንም እንደ ተናገርህ አድርግ።
1 ሳሙኤል 1:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባልዋም ሕልቃና፥ “በዐይንሽ ደስ ያሰኘሽን አድርጊ፤ ጡትም እስኪተው ድረስ ተቀመጪ፤ ብቻ እግዚአብሔር ከአፍሽ የወጣውን ያጽና” አላት። ሴቲቱም ልጅዋን እያጠባች ጡት እስኪተው ድረስ ተቀመጠች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ባሏ ሕልቃናም፣ “መልካም መስሎ የታየሽን አድርጊ፤ ጡት እስክታስጥዪው ድረስ እዚሁ ቈዪ፤ ብቻ እግዚአብሔር ቃሉን ያጽናልሽ” አላት። ስለዚህ ሐና ሕፃኑን ጡት እስክታስጥለው ድረስ እያጠባችው በቤቷ ተቀመጠች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባሏ ሕልቃናም፥ “መልካም መስሎ የታየሽን አድርጊ፤ ጡት እስክታስጥይው ድረስ እዚሁ ቆይ፤ ብቻ ጌታ ቃሉን ያጽናልሽ” አላት። ስለዚህ ሴቲቱ ሕፃኑን ጡት እስክታስጥለው ድረስ እያጠባችው በቤቷ ተቀመጠች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕልቃናም “ጥሩ ነው፤ መልካም መስሎ የታየሽን አድርጊ፤ ጡት እስክታስጥይውም ድረስ በቤት መቈየት ትችያለሽ፤ እግዚአብሔር የሰጠሽን የተስፋ ቃል ይፈጽምልሽ” ሲል መለሰላት፤ ስለዚህም ሐና በቤት ተቀምጣ ልጇን ታሳድግ ጀመር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባልዋም ሕልቃና፦ በዓይንሽ ደስ ያሰኘሽን አድርጊ፥ ጡትም እስኪተው ድረስ ተቀመጪ፥ ብቻ እግዚአብሔር ቃሉን ያጽና አላት። ሴቲቱም ልጅዋን እያጠባች ጡት እስኪተው ድረስ በቤትዋ ተቀመጠች። |
አቤቱ ሁሉን የምትገዛ የእስራኤል አምላክ ሆይ፥ አሁንም ለባሪያህና ለቤቱ የተናገርኸውን ለዘለዓለም አጽናው፤ አሁንም እንደ ተናገርህ አድርግ።
ልጄንም አጠባ ዘንድ በማለዳ ብነሣ፥ ያን የሞተውን ልጅ አገኘሁ፤ ነገር ግን ብርሃን በሆነ ጊዜ ተመለከትሁት፤ እነሆም፥ የወለድሁት ልጄ አልነበረም።”
የባርያውን ቃል ያጸናል፤ የመልእክተኞቹንም ምክር ይፈጽማል። ኢየሩሳሌምን፦ የሰው መኖሪያ ትሆኛለሽ፤ የይሁዳንም ከተሞች ትታነጻላችሁ፤ ምድረ በዳዎችዋም ይለመልማሉ፤” ይላል፤
ባልዋ ግን በሰማበት ቀን ስእለቷን ቢከለክላት፥ ስለ ስእለቷ ወይም ራስዋን ስላሰረችበት መሐላ ከአፍዋ የወጣው ነገር አይጸናም፤ ባልዋ ከልክሏታል፤ እግዚአብሔርም ያነጻታል።
ከዚህም በኋላ ይህን ሲናገር ከሕዝቡ መካከል አንዲት ሴት ድምፅዋን አሰምታ፥ “የተሸከመችህ ማኅፀን ብፅዕት ናት፤ የጠባሃቸው ጡቶችም ብፁዓት ናቸው” አለችው።
ሳኦልም፥ “ፍልስጥኤማውያንን በሌሊት ተከትለን እንውረድ፤ እስኪነጋም ድረስ እንበዝብዛቸው፤ አንድ ሰው እንኳ አናስቀርላቸው” አለ። እነርሱም፥ “ደስ የሚያሰኝህን ሁሉ አድርግ” አሉት። ካህኑም፥ “ወደ እግዚአብሔር እንቅረብ” አለ።
እስራኤልንም ሁሉ፥ “እናንተ አንድ ወገን ትሆናላችሁ፤ እኔና ልጄ ዮናታንም አንድ ወገን እንሆናለን” አለ። ሕዝቡም ሳኦልን፥ “ደስ የሚያሰኝህን አድርግ” አሉት።