1 ነገሥት 7:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መስኮቶቹም በሦስት ወገን ነበሩ፤ መስኮቶቹም በሦስት ወገን ፊት ለፊት ይተያዩ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መስኮቶቹም ከፍ ብለው የተሠሩ በሦስት ምድብ የተከፈሉና ትይዩ ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ትይዩ የሆኑት የሕንጻው ሁለት ግንቦች እያንዳንዳቸው በመደዳ ሦስት ሦስት መስኮቶች ነበሩአቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ትይዩ የሆኑት የሕንጻው ሁለት ግንቦች እያንዳንዳቸው በመደዳ ሦስት ሦስት መስኮቶች ነበሩአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መስኮቶቹም በሦስት ተራ ነበሩ፤ መስኮቶቹም ፊት ለፊት ይተያዩ ነበሩ። |
በአዕማዱም ላይ በነበሩ አግዳሚዎች ቤቱ በዋንዛ ሳንቃ ተሸፍኖ ነበር፤ አዕማዱም በአንዱ ወገን ዐሥራ አምስት፥ በአንዱ ወገን ዐሥራ አምስት የሆኑ አርባ አምስት ነበሩ።
ደጆቹ፥ መቃኖቹና የታችኛውና የላይኛው መድረኮች ሁሉ አራት ማዕዘን ነበሩ፤ መስኮቶቹም በሦስት ወገን ሆነው ፊት ለፊት ይተያዩ ነበር።
በዕቃ ቤቶቹም በበሩ ውስጥ በዙሪያው በነበሩትም በግንቡ አዕማድ የዐይነ ርግብ መስኮቶች ነበሩባቸው፤ ደግሞም በደጀ ሰላሙ ውስጥ በዙሪያው መስኮቶች ነበሩ፤ በግንቡም አዕማድ ሁሉ ላይ የዘንባባ ዛፍ ተቀርጾባቸው ነበር።
መስኮቶቹም፥ መዛነቢያዎቹም፥ የዘንባባ ዛፎቹም ወደ ምሥራቅ እንደሚመለከተው በር ልክ ነበሩ፤ ወደ እርሱም የሚያደርሱ ሰባት ደረጃዎች ነበሩ፤ መዛነቢያዎቹም በፊቱ ነበሩ።
በእርሱና በመዛነቢያዎቹም ዙሪያ እንደ እነዚያ መስኮቶች የሚመስሉ መስኮቶች ነበሩ፤ ርዝመቱ አምሳ ክንድ፥ ወርዱም ሃያ አምስት ክንድ ነበረ።
እንደዚያውም መጠን አድርጎ የዕቃ ቤቶቹንና የግንቡን አዕማድ፥ መዛነቢያዎቻቸውንም ለካ፤ በእርሱና በመዛነቢያዎቹም ዙሪያ መስኮቶች ነበሩ፤ ርዝመቱ አምሳ ክንድ፥ ወርዱም ሃያ አምስት ክንድ ነበረ።
እንደዚያም መጠን የዕቃ ቤቶቹንና የግንቡን አዕማድ፥ መዛነቢያዎቹንም ለካ፤ በእርሱና በመዛነቢያዎቹም ዙሪያ መስኮቶች ነበሩ፤ ርዝመቱም አምሳ ክንድ፥ ወርዱም ሃያ አምስት ክንድ ነበረ።
የዕቃ ቤቶቹንና የግንቡን አዕማድ፥ መዛነቢያዎቹንም ለካ፤ በዙሪያውም መስኮቶች ነበሩበት፤ ርዝመቱም አምሳ ክንድ፥ ወርዱም ሃያ አምስት ክንድ ነበረ።
በደጀ ሰላሙም በሁለቱ ወገን በዚህና በዚያ የዐይነ ርግብ መስኮቶችና የተቀረጹ የዘንባባ ዛፎች ነበሩበት፤ የመቅደሱም ጓዳዎችና የእንጨቱ መድረክ እንዲሁ ነበሩ።