1 ነገሥት 4:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዋሊያና ከሚዳቋ፥ ከበረሃ ፍየልና ከሰቡ ወፎች በቀር ዐሥር ፍሪዳዎች፥ ሃያም የተሰማሩ በሬዎች፥ አንድ መቶም በጎች ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዐሥር ቅልብ ሰንጋዎች፣ ሃያ ግጦሽ መሬት ላይ የሚውሉ በሬዎች፣ መቶ በግና ፍየል እንዲሁም ዋሊያ፣ ሚዳቋ፣ የበረሓ ፍየልና ምርጥ አዕዋፍ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በበረት ውስጥ እየተመገቡ የደለቡ ዐሥር ሰንጋዎችና በግጦሽ መስክ ተሰማርተው የተመገቡ ኻያ ፍሪዳዎችና አንድ መቶ በጎች፥ ከዚህም ሌላ አጋዘኖች፥ የሜዳ ፍየሎች፥ ሚዳቋዎችና ምርጥ ወፎች ያስፈልጉት ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በበረት ውስጥ እየተመገቡ የደለቡ ዐሥር ሰንጋዎችና በግጦሽ መስክ ተሰማርተው የተመገቡ ኻያ ፍሪዳዎችና አንድ መቶ በጎች፥ ከዚህም ሌላ አጋዘኖች፥ የሜዳ ፍየሎች፥ ሚዳቋዎችና ምርጥ ወፎች ያስፈልጉት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዋላና ከሚዳቋ ከበረሃ ፍየልና ከሰቡ ወፎች በቀር ዐሥር ፍሪዳዎች ሃያም የተሰማሩ በሬዎች አንድ መቶም በጎች ነበረ። |
ከወንዙ ወዲህ ባሉት ነገሥታት ሁሉ፥ ከወንዙም ወዲህ ባለው ሀገር ሁሉ ላይ ከቲላሳ ጀምሮ እስከ ጋዛ ድረስ ነግሦ ነበር፤ በዙሪያውም ባለው በሁሉ ወገን ሰላም ሆኖለት ነበር።
ወንዶችና ሴቶች አገልጋዮችን ገዛሁ፤ በቤት የተወለዱ አገልጋዮችም ነበሩኝ፤ ከእኔ አስቀድመው በኢየሩሳሌም ከነበሩት ሁሉ ይልቅ ብዙ የበጎችና የከብቶች መንጋዎች ነበሩኝ።