1 ነገሥት 4:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የነበሩትም አለቆች እነዚህ ናቸው፥ የሳዶቅ ልጅ ካህኑ ዓዛርያስ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዋና ዋናዎቹ ሹማምቱም እነዚህ ነበሩ፤ የሳዶቅ ልጅ ዓዛርያስ፣ ካህን፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሾማቸው ባለ ሥልጣኖች ከዚህ የሚከተሉት ናቸው፤ እነርሱም፦ ዓዛርያስ የተባለው የሳዶቅ ልጅ፦ ካህን፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሾማቸው ባለሥልጣኖች ከዚህ የሚከተሉት ናቸው፥ እነርሱም፦ ዓዛርያስ የተባለው የሳዶቅ ልጅ፦ ካህን፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የነበሩትም አለቆች እነዚህ ናቸው፤ የሳዶቅ ልጅ ካህኑ ዓዛርያስ፥ |
አንተም ከሕዝቡ ሁሉ ኀያላን ሰዎችን፥ እግዚአብሔርን የሚፈሩትን እውነተኞች ሰዎችን፥ ትዕቢትንም የሚጠሉ ሰዎችን ፈልግ። ከእነርሱም የሺህ አለቆችን፥ የመቶ አለቆችን፥ የአምሳ አለቆችን፥ የዐሥርም አለቆችን ሹምላቸው።
እግዚአብሔር ለቤተ ክርስቲያን የሾማቸው አስቀድሞ ሐዋርያትን፥ ሁለተኛም ነቢያትን፥ ሦስተኛም መምህራንን፥ ከዚህም በኋላ ተአምራትና ኀይል ማድረግ የተሰጣቸውን፥ ቀጥሎም የመፈወስ ሀብት የተሰጣቸውን፥ የመርዳትም ሀብት የተሰጣቸውን፥ የመምራትና ቋንቋን የመናገር ሀብት የተሰጣቸውን ነው።