1 ነገሥት 3:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባሪያህም ያለው አንተ በመረጥኸው ሕዝብህ፥ ስለ ብዛቱም ይቈጠር ዘንድ በማይቻል በታላቅ ሕዝብ መካከል ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ባሪያህ አንተ በመረጥኸው ሕዝብ፣ ከብዛቱም የተነሣ ሊቈጠር በማይችል ታላቅ ሕዝብ መካከል ይገኛል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነሆ እኔ የአንተ እንዲሆን በመረጥከውና ከብዛቱ የተነሣ ሊቆጠር በማይችል ሕዝብ መካከል እገኛለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነሆ እኔ የአንተ እንዲሆን በመረጥከውና ከብዛቱ የተነሣ ሊቈጠር በማይችል ሕዝብ መካከል እገኛለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባሪያህም ያለው አንተ በመረጥኸው ሕዝብህ ስለ ብዛቱም ይቈጠርና ይመጠን ዘንድ በማይቻል በታላቅ ሕዝብ መካከል ነው። |
ወደ ሜዳም አወጣውና “ወደ ላይ ወደ ሰማይ ተመልከት፤ ልትቈጥራቸው ትችል እንደሆነ ከዋክብትን ቍጠራቸው። ዘርህም እንደዚሁ ነው” አለው።
ዘርህንም እንደ ሰማይ ከዋክብትና በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ ፈጽሞ አበዛዋለሁ፤ ዘርህም የጠላት ሀገሮችን ይወርሳሉ፤
ዳዊትም ኢዮአብንና የሕዝቡን አለቆች ሁሉ፥ “ሂዱ፥ ከቤርሳቤህ ጀምሮ እስከ ዳን ድረስ እስራኤልን ቍጠሩ፤ ድምራቸውንም አውቅ ዘንድ አስታውቁኝ” አላቸው።
ወደ እናንተም እመለከታለሁ፤ አባዛችኋለሁ፤ ከፍ ከፍም አደርጋችኋለሁ፤ ቃል ኪዳኔንም ከእናንተ ጋር አጸናለሁ።
እግዚአብሔር ለእርሱ ሕዝብ ያደርጋችሁ ዘንድ ተቀብሎአችኋልና፥ እግዚአብሔር ስለ ታላቅ ስሙ ሕዝቡን አይተውም።