1 ነገሥት 22:44 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢዮሣፍጥም ከእስራኤል ንጉሥ ጋር ታረቀ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም ኢዮሣፍጥ ከእስራኤል ንጉሥ ጋራ በሰላም ኖረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህም ሕዝቡ በእነዚያ ቦታዎች መሥዋዕት ማቅረብና ዕጣን የማጠን ተግባሩን አልተወም ነበር፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢዮሣፍጥም ከእስራኤል ንጉሥ ጋር ሰላም መሥርቶ ይኖር ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢዮሣፍጥም ከእስራኤል ንጉሥ ጋር ታረቀ። |
ሰሎሞንም እግዚአብሔርን ይወድድ ነበር፤ በአባቱም በዳዊት ሥርዐት ይሄድ ነበር፤ ነገር ግን በኮረብታው ላይ ይሠዋና ያጥን ነበር።
በእስራኤልም ንጉሥ በአክዓብ ልጅ በኢዮራም በአምስተኛው ዓመት የይሁዳ ንጉሥ የኢዮሣፍጥ ልጅ ኢዮራም በይሁዳ ነገሠ።
የአክዓብንም ልጅ አግብቶ ነበርና የአክዓብ ቤት እንዳደረገ በእስራኤል ነገሥታት መንገድ ሄደ፤ በእግዚአብሔርም ፊት ክፉ አደረገ።
ነቢዩ የአናኒ ልጅ ኢዩ ሊገናኘው ወጣ፤ ንጉሡንም ኢዮሣፍጥን፥ “ኀጢአተኛውን ታግዛለህን? ወይስ እግዚአብሔር የሚጠላውን ትወድዳለህን? ስለዚህም ነገር ከእግዚአብሔር ዘንድ ቍጣ መጥቶብሃል።
የአክዓብንም ልጅ አግብቶ ነበርና የአክዓብ ቤት እንዳደረገ በእስራኤል ነገሥታት መንገድ ሄደ፤ በእግዚአብሔርም ፊት ክፉ አደረገ።
በተራሮችም ላይ ስላጠኑ፥ በኮረብቶችም ላይ ስለ አሽሟጠጡኝ ስለዚህ አስቀድመው የሠሩትን ሥራቸውን በብብታቸው እሰፍራለሁ።
ተጠራጣሪዎች አትሁኑ፤ ወደማያምኑ ሰዎች አንድነትም አትሂዱ፤ ጽድቅን ከኀጢአት ጋር አንድ የሚያደርጋት ማን ነው? ብርሃንንስ ከጨለማ ጋር የሚቀላቅል ማን ነው?