ዳግመኛም ወልደ አዴር እንዲህ ብሎ ወደ እርሱ ላከ፥ “ሕዝቤና ሠራዊቴ ሁሉ ሀገርህን ሰማርያን ባያጠፉት፥ የቀበሮም ማደሪያ ባያደርጉት አማልክት እንዲህ ያድርጉብኝ፤ እንዲህም ይግደሉኝ።”
1 ነገሥት 21:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለወልደ አዴር መልእክተኞችም፥ “ለጌታችሁ፦ ለእኔ አገልጋይህ በመጀመሪያ የላክህብኝን ሁሉ አደርጋለሁ፤ ይህን ነገር ግን አደርገው ዘንድ አይቻለኝም” በሉት አላቸው። መልክእክተኞችም ተመልሰው ይህን ነገር ነገሩት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በደብዳቤዎቹም ላይ እንዲህ ስትል ጻፈች፤ “የአንድ ቀን ጾም ዐውጁ፤ ናቡቴንም በሕዝቡ መካከል ከፍ ባለ ቦታ ላይ አስቀምጡት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለአዴርም ልጅ መልአክተኞች፦ “ለጌታዬ ለንጉሥ፥ ለእኔ ለባርያህ በመጀመሪያ የላክህብኝ ሁሉ አደርጋለሁ፥ ይህ ግን አደርገው ዘንድ አይቻለኝም በሉት” አላቸው፤ መልእክተኞችም ተመልሰው ይህን አወሩለት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደብዳቤውም እንዲህ የሚል ነበር፦ “የአንድ ቀን ጾም ዐውጁ፤ ሕዝቡንም በአንድነት ሰብስቡ፤ ለናቡቴም የክብር ቦታ ስጡት፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለወልደ አዴርም መልአክተኞች፦ ለጌታዬ ለንጉሥ፦ ለእኔ ለባሪያህ በመጀመሪያ የላክህብኝ ሁሉ አደርጋለሁ፤ ይህ ግን አድርገው ዘንድ አይቻለኝም በሉት አላቸው። መልእክተኞችም ተመልሰው ይህን አወሩለት። |
ዳግመኛም ወልደ አዴር እንዲህ ብሎ ወደ እርሱ ላከ፥ “ሕዝቤና ሠራዊቴ ሁሉ ሀገርህን ሰማርያን ባያጠፉት፥ የቀበሮም ማደሪያ ባያደርጉት አማልክት እንዲህ ያድርጉብኝ፤ እንዲህም ይግደሉኝ።”
እነሆ፥ ለጠብና ለክርክር ትጾማላችሁ፤ ድሃውንም በጡጫ ትማታላችሁ፤ በምትጮኹበት ጊዜ ድምፃችሁ እንዲሰማ ለእኔ ትጾማላችሁን? ድምፃችሁንም ወደ ላይ ታሰሙ ዘንድ ዛሬ እንደምትጾሙት አትጾሙም።
ወደ ቤተ ልሔምም እነርሱን ሰድዶ “ሂዱ፤ ስለ ሕፃኑ በጥንቃቄ መርምሩ፤ ባገኛችሁትም ጊዜ እኔ ደግሞ መጥቼ እንድሰግድለት ንገሩኝ” አላቸው።
“እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን! መንግሥተ ሰማያትን በሰው ፊት ስለምትዘጉ ወዮላችሁ፤ እናንተ አትገቡም፤ የሚገቡትንም እንዳይገቡ ትከለክላላችሁ።
ጌታችን ኢየሱስንም ከቀያፋ ወደ ፍርድ አደባባይ ወሰዱት፤ አይሁድ ግን ፈጽሞ ስለ ነጋ የፋሲካውን በግ ሳይበሉ እንዳይረክሱ ወደ ፍርድ አደባባይ አልገቡም።