እርሱም ለአገልጋዮቹ፥ “እነሆ፥ የእስራኤል ነገሥታት መሓሪዎች ነገሥታት እንደ ሆኑ አውቃለሁ፤ በወገባችን ማቅ እንታጠቅ፤ በራሳችንም ገመድ እንጠምጥም፤ ወደ እስራኤልም ንጉሥ እንሂድ፤ ምናልባት ሰውነታችንን ያድናት ይሆናል” አላቸው።
ባሪያዎቹም፦ እነሆ፥ የእስራኤል ቤት ነገሥታት መሐሪዎች እንደ ሆኑ ሰምተናል፤ በወገባችን ማቅ እንታጠቅ፥ በራሳችንም ገመድ እንጠምጥም፥ ወደ እስራኤልም ንጉሥ እንውጣ፤ ምናልባት ነፍስህን ይምራታል አሉት።