La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ነገሥት 19:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ከዚህ በኋላ ኤል​ያስ ተነ​ሥቶ፥ እነሆ፥ በራሱ አጠ​ገብ የተ​ጋ​ገረ እን​ጎ​ቻና በማ​ሰሮ ውኃ አገኘ። በላም፤ ጠጣም፤ ተመ​ል​ሶም ተኛ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ዘወር ብሎ ሲመለከትም፣ እነሆ፣ በፍም የተጋገረ ዕንጐቻና አንድ ገንቦ ውሃ ከራስጌው አገኘ፤ ከበላና ከጠጣም በኋላ ተመልሶ ተኛ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ኤልያስም ተነሥቶ ዙሪያውን በተመለከተ ጊዜ በድንጋይ ሙቀት የበሰለ የዳቦ ሙልሙልና አንድ ገንቦ ውሃ በራስጌው ተቀምጦ አየ፤ ከበላና ከጠጣም በኋላ ተመልሶ ተኛ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ኤልያስም ተነሥቶ ዙሪያውን በተመለከተ ጊዜ በድንጋይ ሙቀት የበሰለ የዳቦ ሙልሙልና አንድ ገንቦ ውሃ በራስጌው ተቀምጦ አየ፤ ከበላና ከጠጣም በኋላ ተመልሶ ተኛ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሲመለከትም፥ እነሆ፥ በራሱ አጠገብ የተጋገረ እንጎቻና በማሰሮ ውሃ አገኘ። በላም፤ ጠጣም፤ ተመልሶም ተኛ።

Ver Capítulo



1 ነገሥት 19:6
13 Referencias Cruzadas  

ከፈ​ፋው ትጠ​ጣ​ለህ፤ ቁራ​ዎ​ችም በዚያ ይመ​ግ​ቡህ ዘንድ አዝ​ዣ​ለሁ።” ሄደም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዳ​ዘ​ዘው አደ​ረገ።


ቁራ​ዎ​ችም በየ​ጥ​ዋ​ቱና በየ​ማ​ታው እን​ጀ​ራና ሥጋ ያመ​ጡ​ለት ነበር፤ ከፈ​ፋ​ውም ይጠጣ ነበር።


በደ​ድ​ሆ​ውም ዛፍ በታች ተኛ፤ እን​ቅ​ል​ፍም አን​ቀ​ላፋ፤ እነ​ሆም፥ መል​አክ ዳሰ​ሰ​ውና፥ “ተነ​ሥ​ተህ ብላ” አለው።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ ደግሞ ሁለ​ተኛ ጊዜ መጥቶ ዳሰ​ሰ​ውና፥ “የም​ት​ሄ​ድ​በት መን​ገድ ሩቅ ነውና ተነ​ሥ​ተህ ብላ” አለው።


ከቍ​ጣህ ፊት የተ​ነሣ ለሥ​ጋዬ ድኅ​ነት የለ​ውም፤ ከኀ​ጢ​አ​ቴም ፊት የተ​ነሣ ለአ​ጥ​ን​ቶቼ ሰላም የላ​ቸ​ውም።


እርሱ ከፍ ባለ በጽ​ኑዕ ዓለት ዋሻ ይኖ​ራል፤ እን​ጀ​ራም ይሰ​ጠ​ዋል፤ ውኃ​ውም የታ​መ​ነች ትሆ​ና​ለች።


አንዲት ሴት ዋጋው እጅግ የበዛ ሽቱ የሞላው የአልባስጥሮስ ብልቃጥ ይዛ ወደ እርሱ ቀረበች፤ በማዕድም ተቀምጦ ሳለ በራሱ ላይ አፈሰሰችው።


ያን ጊዜ ዲያቢሎስ ተወው፤ እነሆም፥ መላእክት ቀርበው ያገለግሉት ነበር።


ይህንስ ሁሉ አሕዛብ ይፈልጋሉ፤ ይህ ሁሉ እንዲያስፈልጋችሁ የሰማዩ አባታችሁ ያውቃልና።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ልጆች ሆይ አን​ዳች የሚ​በላ ነገር አላ​ች​ሁን?” አላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም፥ “የለም” አሉት።


ወደ ምድ​ርም በወ​ረዱ ጊዜ ፍሙ መርቶ፥ ዓሣም በላዩ ሆኖ፥ እን​ጀ​ራም ተሠ​ርቶ አገኙ።