ኤልያስም፥ “እግዚአብሔርን ትታችሁ በዓሊምን የተከተላችሁ፥ አንተና የአባትህ ቤት ናችሁ እንጂ እኔስ እስራኤልን አልገለባብጥም።
1 ነገሥት 16:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሰማርያም በሠራው በበዓል ቤት ውስጥ ለበዓል መሠዊያን ሠራ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰማርያ ላይ በሠራውም የበኣል ቤተ ጣዖት ለበኣል መሠዊያ አቆመለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሰማርያም ለባዓል ቤተ መቅደስ አሳንጾ መሠዊያ ሠራለት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሰማርያም ለባዓል ቤተ መቅደስ አሳንጾ መሠዊያ ሠራለት፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሰማርያም በሠራው በበኣል ቤት ውስጥ ለበኣል መሠዊያ አቆመ። |
ኤልያስም፥ “እግዚአብሔርን ትታችሁ በዓሊምን የተከተላችሁ፥ አንተና የአባትህ ቤት ናችሁ እንጂ እኔስ እስራኤልን አልገለባብጥም።
ኢዩም ወደ እስራኤል ሀገሮች ሁሉ ላከ፤ የበዓልም አገልጋዮች ሁሉ፥ ካህናቱም ሁሉ፥ ነቢያቶቹም ሁሉ መጡ፤ ከእነርሱም ሳይመጣ የቀረ አንድ ሰው እንኳ አልነበረም። ሁሉም ወደ በዓል ቤት ገቡ፤ የበዓልንም ቤት ከዳር እስከ ዳር ድረስ ሞሉት።
በእግዚአብሔርም ፊት ክፉ አደረገ፤ ነገር ግን እንደ አባቱና እንደ እናቱ አልነበረም፤ አባቱም ያሠራውን የበዓልን ምስል አጠፋ።