በይሁዳም ንጉሥ በአሳ በሦስተኛው ዓመት የአኪያ ልጅ ባኦስ በእስራኤል ሁሉ ላይ በቴርሣ ንጉሥ ሆኖ ሃያ አራት ዓመት ነገሠ።
1 ነገሥት 16:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔርም ቃል ስለ ባኦስ እንዲህ ብሎ ወደ አናኒ ልጅ ወደ ኢዩ መጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም የእግዚአብሔር ቃል በባኦስ ላይ እንዲህ ሲል ወደ አናኒ ልጅ ወደ ኢዩ መጣ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሐናኒ ልጅ በሆነው በነቢዩ ኢዩ አማካይነት ጌታ ስለ ባዕሻ የተናገረው ቃል ይህ ነው፦ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሐናኒ ልጅ በሆነው በነቢዩ ኢዩ አማካይነት እግዚአብሔር ስለ ባዕሻ የተናገረው ቃል ይህ ነው፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔርም ቃል በባኦስ ላይ እንዲህ ብሎ ወደ አናኒ ልጅ ወደ ኢዩ መጣ። |
በይሁዳም ንጉሥ በአሳ በሦስተኛው ዓመት የአኪያ ልጅ ባኦስ በእስራኤል ሁሉ ላይ በቴርሣ ንጉሥ ሆኖ ሃያ አራት ዓመት ነገሠ።
በእጁም ሥራ ያስቈጣው ዘንድ፥ እንደ ኢዮርብዓም ቤት በእግዚአብሔር ፊት ስላደረገው ክፋት ሁሉ እርሱንም ስለ ገደለው፥ የእግዚአብሔር ቃል በባኦስና በቤቱ ላይ ወደ አናኒ ልጅ ወደ ነቢዩ ኢዩ መጣ።
እግዚአብሔርም፥ “ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፤ ለአባቶቻችሁም እንዳዘዝሁት፥ በባሪያዎቼ በነቢያት የላክሁላችሁን ትእዛዜንና ሥርዐቴን፥ ሕጌንም ሁሉ ጠብቁ” ብሎ በነቢዩ ሁሉና በባለ ራእዩ አፍ ሁሉ በእስራኤልና በይሁዳ መሰከረ።
ነቢዩ የአናኒ ልጅ ኢዩ ሊገናኘው ወጣ፤ ንጉሡንም ኢዮሣፍጥን፥ “ኀጢአተኛውን ታግዛለህን? ወይስ እግዚአብሔር የሚጠላውን ትወድዳለህን? ስለዚህም ነገር ከእግዚአብሔር ዘንድ ቍጣ መጥቶብሃል።
የቀረውም የፊተኞቹና የኋለኞቹ የኢዮሣፍጥ ነገሮች፥ እነሆ የእስራኤልን ነገሥታት ታሪክ በጻፈው በአናኒ ልጅ በነቢዩ በኢዩ ታሪክ ተጽፈዋል።
ታላቅና ኀያል አምላክ ሆይ! ለብዙ ሺህ ምሕረትን ታደርጋለህ፤ የአባቶችንም በደል ከእነርሱ በኋላ በልጆቻቸው ብብት ትመልሳለህ።