ነቢዩም የእግዚአብሔርን ሰው ሬሳ አነሣ፤ በአህያውም ላይ ጫነው፤ ነቢዩም በራሱ መቃብር ይቀብረው ዘንድ ወደ ገዛ ከተማው አመጣው፤
1 ነገሥት 13:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዋይ ዋይ፥ ወንድሜ ሆይ፥ እያሉም አለቀሱለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ሬሳውን በራሱ መቃብር ቀበረው፤ “ዋይ ወንድሜን” እያሉም አለቀሱለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በገዛ ራሱም ቤተሰብ መቃብር ቀበረው፤ እነርሱም “ወንድሜ ሆይ! ወንድሜ ሆይ!” እያሉ አለቀሱለት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሽማግሌውም ነቢይ በገዛ ራሱ ቤተሰብ መቃብር ቀበረው፤ እነርሱም “ወንድሜ ሆይ! ወንድሜ ሆይ!” እያሉ አለቀሱለት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሬሳውንም በገዛ መቃብሩ አኖረው፤ “ዋይ! ዋይ! ወንድሜ ሆይ!” እያሉ አለቀሱለት። |
ነቢዩም የእግዚአብሔርን ሰው ሬሳ አነሣ፤ በአህያውም ላይ ጫነው፤ ነቢዩም በራሱ መቃብር ይቀብረው ዘንድ ወደ ገዛ ከተማው አመጣው፤
ደንገጡሮችሽም ሊቀበሉሽ ይወጣሉ፤ ልጅሽም ሞተ ይሉሻል፥ እስራኤልም ሁሉ ያለቅሱለታል፤ ይቀብሩትማል፤ በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ዘንድ በኢዮርብዓም ቤት በዚህ ልጅ መልካም ነገር ተገኝቶበታልና ከኢዮርብዓም እርሱ ብቻ ይቀበራል።
“ይህ የማየው የተቀበረ ነገር ምንድን ነው?” አለ የዚያችም ከተማ ሰዎች፥ “ከይሁዳ መጥቶ በቤቴል መሠዊያ ላይ ይህን ያደረግኸውን ነገር የተናገረው የእግዚአብሔር ሰው መቃብር ነው” ብለው ነገሩት።
ስለዚህ እግዚአብሔር ስለ ይሁዳ ንጉሥ ስለ ኢዮስያስ ልጅ ስለ ኢዮአቄም እንዲህ ይላል፥ “ወንድሜ ሆይ፥ ወዮ! ጌታዬ ሆይ፥ ወዮ! እያለ የሚያለቅስለት ለሌለው ለዚያ ሰው ወዮለት!