የሁለቱም ዐይኖች ተከፈቱ፤ እነርሱም ዕራቁታቸውን እንደ ሆኑ ዐወቁ፤ አፈሩም፤ የበለስንም ቅጠሎች ሰፍተው ለእነርሱ ለራሳቸው ግልድም አደረጉ።
1 ነገሥት 13:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከይሁዳም የመጣውን የእግዚአብሔርን ሰው እንዲህ አለው፥ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በእግዚአብሔር ቃል ላይ አምፀሃልና፥ አምላክህ እግዚአብሔርም ያዘዘህን ትእዛዝ አልጠበቅህምና፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከይሁዳ ለመጣውም የእግዚአብሔር ሰው፣ “እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፣ ‘የእግዚአብሔርን ቃል አቃልለሃል፤ አምላክህ እግዚአብሔር የሰጠህንም ትእዛዞች አልጠበቅህም፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከይሁዳ ለመጣው ለእግዚአብሔር ሰው እንዲህ አለው፤ “ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘ጌታ አምላክህ ያዘዘህን ትእዛዝ ባለመታዘዝ የጌታን ቃል አላከበርክም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከይሁዳ ለመጣው የእግዚአብሔር ሰው እንዲህ አለው፤ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ‘አምላክህ እግዚአብሔር ያዘዘህን ትእዛዝ ባለመታዘዝ የእግዚአብሔርን ቃል አላከበርክም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከይሁዳም ወደ መጣው ወደ እግዚአብሔር ሰው “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ‘በእግዚአብሔር አፍ ላይ ዐምፀሃልና፥ አምላክህም እግዚአብሔር ያዘዘህን ትእዛዝ አልጠበቅህምና፥ |
የሁለቱም ዐይኖች ተከፈቱ፤ እነርሱም ዕራቁታቸውን እንደ ሆኑ ዐወቁ፤ አፈሩም፤ የበለስንም ቅጠሎች ሰፍተው ለእነርሱ ለራሳቸው ግልድም አደረጉ።
ጋድም ወደ ዳዊት መጥቶ፥ “የሦስት ዓመት ራብ በሀገርህ ላይ ይምጣብህን? ወይስ ጠላቶችህ እያሳደዱህ ሦስት ወር ከእነርሱ ትሸሽን? ወይስ የሦስት ቀን ቸነፈር በሀገርህ ላይ ይሁን? የሚሻልህን ምረጥ። አሁንም ለላከኝ ምን መልስ እንደምሰጥ አስብና መርምር” ብሎ ነገረው።
እግዚአብሔርም በዖዛ ላይ ተቈጣ፤ እግዚአብሔርም በዚያው ቀሠፈው። በእግዚአብሔርም ታቦት አጠገብ በእግዚአብሔር ፊት በዚያው ሞተ።
በዚያ እንጀራ አትብላ፥ ውኃም አትጠጣ፤ በመጣህበት መንገድም አትመለስ ብሎ እግዚአብሔር በቃሉ አዝዞኛልና” አለው።
ተመልሰህም፦ እንጀራ አትብላ፥ ውኃም አትጠጣ ባለህ ስፍራ እንጀራ በልተሃልና፥ ውኃም ጠጥተሃልና ሬሳህ ወደ አባቶችህ መቃብር አይገባም።”
ክፋትሽ ይገሥጽሻል፤ ክዳትሽም ይዘልፍሻል፤ እኔን መተውሽም ክፉና መራራ ነገር መሆኑን ታውቂያለሽ፤ ትረጂማለሽ” ይላል አምላክሽ እግዚአብሔር፤ “መፈራቴም በአንቺ ዘንድ የለም፤ ይህም ደስ አላሰኘኝም” ይላል አምላክሽ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
ሙሴም አሮንን፥ “እግዚአብሔር፦ ወደ እኔ በሚቀርቡ እመሰገናለሁ፤ በሕዝቡም ሁሉ ፊት እከብራለሁ ብሎ የተናገረው ይህ ነው” አለው፤ አሮንም ደነገጠ።
እግዚአብሔርም ሙሴንና አሮንን፥ “በእስራኤል ልጆች ፊት ትቀድሱኝ ዘንድ በእኔ አላመናችሁምና ስለዚህ ወደ ሰጠኋችሁ ምድር ይህን ማኅበር ይዛችሁ አትገቡም” አላቸው።
የእግዚአብሔርንም ታቦት ባሰባት ጊዜ በበሩ አጠገብ ካለው ከወንበሩ ወደቀ፤ እርሱ ሸምግሎ፥ ደንግዞም ነበርና ጀርባው ተሰብሮ ሞተ። እርሱም በእስራኤል ላይ አርባ ዓመት ፈራጅ ነበረ።