ዮናታንና አኪማሆስም በሮጌል ምንጭ አጠገብ ቆመው ሳለ አንዲት ብላቴና ሄዳ ነገረቻቸው፤ ወደ ከተማ መግባት አልተቻላቸውም ነበርና፤ እነርሱም ሄደው ለንጉሡ ለዳዊት ነገሩት።
1 ነገሥት 1:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አዶንያስም በጎችንና በሬዎችን፥ ጠቦቶችንም በሮጌል ምንጭ አጠገብ ባለችው በዞሔሌት ድንጋይ ዘንድ ሠዋ፤ የንጉሡንም ልጆች ወንድሞቹን ሁሉ፥ የንጉሡንም አገልጋዮች፥ የይሁዳንም ኀያላን ሁሉ ጠራ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም አዶንያስ በዓይንሮጌል አቅራቢያ ባለው የዞሔልት ድንጋይ አጠገብ በጎችን፣ በሬዎችንና የሠቡ ጥጆችን ሠዋ፤ ወንድሞቹን ሁሉ፣ የንጉሡን ልጆች እንዲሁም የቤተ መንግሥቱ ሹማምት የነበሩትን የይሁዳ ሰዎች ሁሉ ጠራ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አዶንያስም በጎችንና በሬዎችን ፍሪዳዎችንም በዔንሮጌል አጠገብ ባለችው በዞሔሌት ድንጋይጋ ሠዋ፥ የንጉሡንም ልጆች ወንድሞቹን ሁሉ፥ የንጉሡንም ባርያዎች፥ የይሁዳን ሰዎች ሁሉ ጠራ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንድ ቀን አዶንያስ “ዔንሮጌል” ተብሎ በሚጠራው የውሃ ምንጭ አጠገብ የዞሔሌት አለት በሚባለው ስፍራ በጎችን፥ በሬዎችንና የሰቡ ወይፈኖችን ዐርዶ መሥዋዕት አቀረበ፤ የንጉሥ ዳዊትን ልጆችና በይሁዳ የሚገኙትን የመንግሥት ባለሥልጣኖች ሁሉ ወደዚህ ወደ መሥዋዕቱ በዓል መጥተው ተካፋዮች እንዲሆኑ ጋበዛቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አዶንያስም በጎችንና በሬዎችን ፍሪዳዎችንም በዓይንሮጌል አጠገብ ባለችው በዞሔሌት ድንጋይ ዘንድ ሠዋ፤ የንጉሡንም ልጆች ወንድሞቹን ሁሉ፥ የንጉሡንም ባሪያዎች፥ የይሁዳን ሰዎች ሁሉ ጠራ። |
ዮናታንና አኪማሆስም በሮጌል ምንጭ አጠገብ ቆመው ሳለ አንዲት ብላቴና ሄዳ ነገረቻቸው፤ ወደ ከተማ መግባት አልተቻላቸውም ነበርና፤ እነርሱም ሄደው ለንጉሡ ለዳዊት ነገሩት።
እርሱም ብዙ በሬዎችንና ጠቦቶችን፥ በጎችንም ሠውቶአል፤ የንጉሡንም ልጆች ሁሉ፥ ካህኑንም አብያታርን፥ የሠራዊቱንም አለቃ ኢዮአብን ጠርቶአል፤ ባሪያህን ሰሎሞንን ግን አልጠራውም።
እርሱ ዛሬ ወርዶ ብዙ በሬዎችንና ጠቦቶችን፥ በጎችንም ሠውቶአል፤ የንጉሡንም ልጆች ሁሉ፥ የሠራዊቱን አለቃ ኢዮአብን፥ ካህኑንም አብያታርን ጠርቶአል፤ እነሆም፥ በፊቱ እየበሉና እየጠጡ፦ አዶንያስ ሺህ ዓመት ይንገሥ ይላሉ።
ደግሞ ሌሎችን ባሮች ልኮ ‘የታደሙትን እነሆ፥ ድግሴን አዘጋጀሁ፤ ኮርማዎቼና የሰቡት ከብቶቼ ታርደዋል፤ ሁሉም ተዘጋጅቶአል፤ ወደ ሰርጉ ኑ፤ በሉአቸው፤’ አለ።
ድንበሩም በአኮር ሸለቆ አራተኛ ክፍል ላይ ይወጣል፤ በአዱሚን ዐቀበት ፊት ለፊት፥ በደቡብ በኩል ወዳለችው ወደ ጌልገላ ይወርዳል፤ ድንበሩም ወደ ፀሐይ ምንጭ ውኃ ያልፋል፤ መውጫውም በሮጌል ምንጭ አጠገብ ነበረ፤
ድንበሩም በሄኖም ሸለቆ ፊት ለፊት ወዳለው ተራራ መጨረሻ ወረደ፤ እርሱም በራፋይም ሸለቆ በሰሜን በኩል ነው፤ ወደ ሄኖም ሸለቆ ወደ ኢያቡስ ዳር በደቡብ በኩል ወረደ፥ ወደ ሮጌል ምንጭም ወረደ።