1 ነገሥት 1:51 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለሰሎሞንም፥ “እነሆ፥ አዶንያስ ንጉሡን ሰሎሞንን ፈርቶ፦ ንጉሡ ሰሎሞን አገልጋዩን በሰይፍ እንዳይገድለኝ ዛሬ ይማልልኝ ብሎ የመሠዊያውን ቀንድ ይዞአል” አሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም፣ ለሰሎሞን፣ “አዶንያስ እነሆ፣ ንጉሥ ሰሎሞንን በመፍራት የመሠዊያውን ቀንድ ይዞ ተማጥኗል፤ እርሱም፣ ‘ባሪያውን በሰይፍ እንዳይገድለው ንጉሡ ሰሎሞን ዛሬውኑ ይማልልኝ’ ብሏል” ብለው ነገሩት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለሰሎሞንም፦ “እነሆ፥ አዶንያስ ንጉሡን ሰሎሞንን ፈርቶ፦ ‘ንጉሡ ሰሎሞን ባርያውን በሰይፍ እንዳይገድለኝ ዛሬ ይማልልኝ’ ብሎ የመሠዊያውን ቀንድ ይዞአል” አሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰዎቹም ሰሎሞንን “አዶንያስ አንተን ከመፍራቱ የተነሣ የመሠዊያውን ቀንዶች ይዞ ‘ከሁሉ በፊት ንጉሥ ሰሎሞን የማይገድለኝ መሆኑን በማረጋገጥ በመሐላ ቃል ይግባልኝ’ በማለት እየተማጠነ ነው” ሲሉ ነገሩት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለሰሎሞንም “እነሆ፥ አዶንያስ ንጉሡን ሰሎሞንን ፈርቶ ‘ንጉሡ ሰሎሞን ባሪያውን በሰይፍ እንዳይገድለኝ ዛሬ ይማልልኝ፤’ ብሎ የመሠዊያውን ቀን ይዞአል፤” አሉት። |
ሰሎሞንም፥ “እርሱ አካሄዱን ያሳመረ እንደ ሆነ ከእርሱ አንዲት ጠጕር እንኳ በምድር ላይ አትወድቅም፤ ነገር ግን ክፋት የተገኘበት እንደ ሆነ ይሞታል” አለ።