1 ነገሥት 1:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቤርሳቤህም አጎንብሳ ለንጉሡ ሰገደች፤ ንጉሡም፥ “ምን ሆንሽ?” አላት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቤርሳቤህም ለጥ ብላ እጅ ከነሣች በኋላ እፊቱ በጕልበቷ ተንበረከከች። ንጉሡም፣ “ምን ትፈልጊያለሽ?” ሲል ጠየቃት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቤርሳቤህም አጎንብሳ ለንጉሡ እጅ ነሣች፥ ንጉሡም፦ “ምን ትፈልጊያለሽ?” አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቤርሳቤህም ወደ መሬት ለጥ ብላ እጅ ነሣች፤ ንጉሡም “ምን ትፈልጊያለሽ?” አላት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቤርሳቤህም አጎንብሳ ለንጉሡ እጅ ነሣች፤ ንጉሡም “ምን ትፈልጊያለሽ?” አለ። |
እርስዋም አለችው፥ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ አንተ ለአገልጋይህ፦ ልጅሽ ሰሎሞን ከእኔ በኋላ ይነግሣል፤ በዙፋኔም ይቀመጣል ብለህ በአምላክህ ምለህልኝ አልነበረምን?
ለንጉሡም፥ “እነሆ፥ ነቢዩ ናታን መጥቶአል” ብለው ነገሩት፤ እርሱም ወደ ንጉሡ ፊት በገባ ጊዜ በግንባሩ በምድር ላይ ተደፍቶ ለንጉሡ እጅ ነሣ።
እርስዋም፥ “አንዲት ትንሽ ልመና እለምንሃለሁ፤ ፊትህን አትመልስብኝ” አለች። ንጉሡም፥ “እናቴ ሆይ! ፊቴን አልመልስብሽምና ለምኚ” አላት።
እርሱም “ምን ትፈልጊያለሽ?” አላት። እርስዋም “እነዚህ ሁለቱ ልጆቼ አንዱ በቀኝህ አንዱም በግራህ በመንግሥትህ እንዲቀመጡ እዘዝ፤” አለችው።
ብላቴናውም በሄደ ጊዜ ዳዊት ከኤርገብ ተነሣ፤ በምድርም ላይ በግንባሩ ተደፋ፤ ሦስት ጊዜም ሰገደ፤ እርስ በእርሳቸውም ተሳሳሙ፤ ለረዥም ሰዓትም ተላቀሱ።
ዳዊትም በዚህ ቃል ሰዎቹን ከለከላቸው። በሳኦልም ላይ ተነሥተው ይገድሉት ዘንድ አልፈቀደላቸውም፤ ሳኦልም ከዋሻው ተነሥቶ መንገዱን ሄደ።
አቤግያም ዳዊትን ባየች ጊዜ ከአህያዋ ላይ ፈጥና ወረደች፤ በዳዊትም ፊት በግንባርዋ ወደቀች፤ ምድርም ነክታ ሰገደችለት።