1 ዮሐንስ 3:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ትእዛዙንም የምንጠብቅና በፊቱ ደስ የሚያሰኘውን የምናደርግ ስለሆንን የምንለምነውን ሁሉ ከእርሱ እናገኛለን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ትእዛዞቹንም ስለምንጠብቅና በፊቱም ደስ የሚያሠኘውን ስለምናደርግ የምንለምነውን ሁሉ ከርሱ እንቀበላለን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ትእዛዛቱን ስለምንጠብቅ፥ በፊቱም ደስ የሚያሰኘውን ስለምናደርግ፥ የምንለምነውን ሁሉ ከእርሱ እናገኛለን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእግዚአብሔርን ትእዛዞች የምንፈጽምና እርሱን ደስ የሚያሰኘውንም የምናደርግ ስለ ሆንን የምንለምነውን ሁሉ ከእርሱ እናገኛለን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ትእዛዙንም የምንጠብቅና በፊቱ ደስ የሚያሰኘውን የምናደርግ ስለሆንን የምንለምነውን ሁሉ ከእርሱ እናገኛለን። |
እግዚአብሔር ከኃጥኣን ፈጽሞ ይርቃል፤ የጻድቃንን ጸሎት ግን ይሰማል። ከዐመፃ ጋር ካለ ብዙ ሀብት ይልቅ፥ ከእውነት ጋር ያለ ጥቂት ሀብት ይሻላል። አካሄዱ ከእግዚአብሔር ይቃናለት ዘንድ፥ የደግ ሰው ልብ እውነትን ያስባል።
እጃችሁን ወደ እኔ ብትዘረጉ፥ ዐይኖችን ከእናንተ እመልሳለሁ፤ ምህላንም ብታበዙ አልሰማችሁም፤ እጆቻችሁ ደምን ተሞልተዋልና።
እርሱም ገና ሲናገር፥ እነሆ፥ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፤ እነሆም፥ ከደመናው “በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት፤” የሚል ድምፅ መጣ።
የምትወዱኝ ብትሆኑ ትእዛዜን ጠብቁ፤ እኔ የአባቴን ትእዛዝ እንደ ጠበቅሁ፥ በፍቅሩም እንደምኖር እናንተም ትእዛዜን ብትጠብቁ በፍቅሬ ትኖራላችሁ።
እኛም እግዚአብሔርን የሚፈራውንና ፈቃዱን የሚያደርገውን እርሱን ይሰማዋል እንጂ ኃጥኣንን እንደማይሰማቸው እናውቃለን።
የቀድሞውንስ ያለ ማወቅ ዘመን እግዚአብሔር አሳልፎታል፤ ዛሬ ግን በመላው ዓለም ንስሓ እንዲገቡ ሰውን ሁሉ አዝዞአል።
ወደ እግዚአብሔር መመለስንና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ማመንን ለአይሁድና ለአረማውያን እየመሰከርሁ፤
ነገር ግን ሁሉ አለኝ፤ ይበዛልኝማል፤ የመዓዛ ሽታና የተወደደ መሥዋዕት የሚሆነውን፥ ለእግዚአብሔርም ደስ የሚያሰኘውን ስጦታችሁን ከአፍሮዲጡ ተቀብዬ አሟልቻለሁ።
ወደ እግዚአብሔር በሚገባችሁ ትሄዱ ዘንድ፥ በበጎ ሥራ ሁሉ ፍሬ እያፈራችሁ፥ እግዚአብሔርንም በማወቅ እያደጋችሁ፥ በሁሉ ደስ ታሰኙት ዘንድ።
የሰላም አምላክ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በፊቱ ደስ የሚያሰኘውን በእናንተ እያደረገ ፈቃዱን ታደርጉ ዘንድ በመልካም ሥራ ሁሉ ፍጹማን ያድርጋችሁ፤ ለእርሱ እስከ ዘለዓለም ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን።