La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ቆሮንቶስ 7:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ለጸ​ሎት እን​ድ​ት​ተጉ ከም​ት​ስ​ማ​ሙ​በት ጊዜ ብቻ በቀር፥ ባልና ሚስት አት​ለ​ያዩ፤ ዳግ​መኛ ሰይ​ጣን ድል እን​ዳ​ያ​ደ​ር​ጋ​ችሁ በአ​ን​ድ​ነት ኑሩ፤ ሰው​ነ​ታ​ችሁ ደካማ ነውና ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በጸሎት ለመትጋት ተስማምታችሁ ለተወሰነ ጊዜ ካልሆነ በቀር፣ እርስ በርሳችሁ አትከላከሉ፤ ራሳችሁን ባለመግዛት ሰይጣን እንዳይፈታተናችሁ እንደ ገና ዐብራችሁ ሁኑ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ለጸሎት ለመትጋት ተስማምታችሁ ለተወሰነ ጊዜ ካልሆነ በቀር፥ እርስ በርሳችሁ አትከላከሉ፤ እንዲሁም ራሳችሁን ስለ አለመግዛት ሰይጣን እንዳይፈታተናችሁ አብራችሁ ሁኑ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በጸሎት ለመትጋት ሁለታችሁም ተስማምታችሁ ለተወሰነ ጊዜ ካልሆነ በቀር በመለያየት አንዱ የሌላውን የጋብቻ መብት አይከልክል። በዚህም ምክንያት ራሳችሁን መቈጣጠር አቅቶአችሁ ሰይጣን እንዳይፈታተናችሁ እንደገና አብራችሁ ሁኑ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ለጸሎት ትተጉ ዘንድ ተስማምታችሁ ለጊዜው ካልሆነ በቀር፥ እርስ በርሳችሁ አትከላከሉ፤ ራሳችሁን ስለ አለመግዛት ሰይጣን እንዳይፈታተናችሁ ደግሞ አብራችሁ ሁኑ።

Ver Capítulo



1 ቆሮንቶስ 7:5
11 Referencias Cruzadas  

ሕዝ​ቡ​ንም፥ “ለሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን ተዘ​ጋጁ፤ ወደ ሴቶ​ቻ​ች​ሁም አት​ቅ​ረቡ” አለ።


ከእ​ር​ስ​ዋም ሌላ ቢያ​ገባ፥ ቀለ​ብ​ዋን፥ ልብ​ስ​ዋ​ንም፥ ለጋ​ብ​ቻ​ዋም ተገ​ቢ​ውን ይስ​ጣት፤ እን​ዳ​ል​በ​ደ​ላ​ትም ምስ​ክር ያሰ​ማ​ባት።


ሕዝ​ቡ​ንም ሰብ​ስቡ፤ ማኅ​በ​ሩ​ንም ቀድሱ፤ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቹ​ንም ጥሩ፤ ጡት የሚ​ጠ​ቡ​ት​ንና ሕፃ​ና​ትን ሰብ​ስቡ፤ ሙሽ​ራው ከእ​ል​ፍኙ፥ ሙሽ​ራ​ዪ​ቱም ከጫ​ጕ​ላዋ ይውጡ።


ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር ቤት ካህናት ለነቢያትም፦ ባለፉት ዓመታት እንዳደረግሁት በአምስተኛው ወር መለየትና ማልቀስ ይገባኛልን? ብለው ይናገሩ ዘንድ ልኮአቸው ነበር።


ይህ ዐይነት ግን ከጸሎትና ከጦም በቀር አይወጣም፤” አላቸው።


እርሱ ግን “ይህ ነገር ለተሰጣቸው ነው እንጂ ለሁሉ አይደለም፤


ያን ጊዜ ኢየሱስ “ሂድ፤ አንተ ሰይጣን ‘ለጌታህ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ’ ተብሎ ተጽፎአልና” አለው።


ሚስት በራ​ስዋ አካል ሥል​ጣን የላ​ትም፤ ሥል​ጣን ለባ​ልዋ ነው እንጂ፤ እን​ዲ​ሁም ባል በራሱ አካል ሥል​ጣን የለ​ውም፤ ሥል​ጣን ለሚ​ስቱ ነው እንጂ።


ስለዚህ እኔ ደግሞ ወደ ፊት እታገሥ ዘንድ ባልተቻለኝ ጊዜ “ፈታኝ ምናልባት ፈትኖአቸዋል፤ ድካማችንም ከንቱ ሆኖአል፤” ብዬ እምነታችሁን ለማወቅ ላክሁ።