ከዚህም በኋላ አብራም የዘጠና ዘጠኝ ዓመት ሰው በሆነ ጊዜ እግዚአብሔር ለአብራም ተገለጠለት፤ እንዲህም አለው “በፊትህ የሄድሁ ፈጣሪህ እግዚአብሔር እኔ ነኝ፤ በፊቴ መልካም አድርግ፤ ንጹሕም ሁን፤
1 ቆሮንቶስ 7:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወንድሞቻችን ሁላችሁም በተጠራችሁበት እንዲሁ በእግዚአብሔር ኑሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወንድሞች ሆይ፤ እያንዳንዱ ሰው በተጠራበት ሁኔታ ከእግዚአብሔር ጋራ ጸንቶ ይኑር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወንድሞች ሆይ! እያንዳንዱ በተጠራ ጊዜ የነበረበት ሁኔታ ምንም ይሁን፥ በእግዚአብሔር ዘንድ ይኑር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ወንድሞቼ ሆይ እያንዳንዱ ሰው በተጠራበት ጊዜ በነበረበት ሁኔታ በእግዚአብሔር ጋር በዚያ ይኑር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወንድሞች ሆይ፥ እያንዳንዱ በተጠራበት እንደዚሁ ሆኖ በእግዚአብሔር ዘንድ ይኑር። |
ከዚህም በኋላ አብራም የዘጠና ዘጠኝ ዓመት ሰው በሆነ ጊዜ እግዚአብሔር ለአብራም ተገለጠለት፤ እንዲህም አለው “በፊትህ የሄድሁ ፈጣሪህ እግዚአብሔር እኔ ነኝ፤ በፊቴ መልካም አድርግ፤ ንጹሕም ሁን፤
ከዚያ ወዲያ ይሄድና ከእርሱ የከፉትን ሰባት ሌሎችን አጋንንት ከእርሱ ጋር ይወስዳል፤ ገብተውም በዚያ ይኖራሉ፤ ለዚያም ሰው ከፊተኛው ይልቅ የኋለኛው ይብስበታል። ለዚህ ክፉ ትውልድ ደግሞ እንዲሁ ይሆንበታል።”
ነገር ግን ሁሉ እግዚአብሔር እንደ አደለው፥ ሁሉም እግዚአብሔር እንደ ጠራው እንዲሁ ይኑር፤ ለአብያተ ክርስቲያናትም ሁሉ እንዲህ ሥርዐት እንሠራለን።
ሕዝቡም ሳኦልን፥ “በውኑ በእስራኤል ዘንድ ታላቅ መድኀኒት ያደረገ ዮናታን ዛሬ ይሞታልን? ይህ አይሁን፤ ዛሬ ለሕዝቡ ከእግዚአብሔር ጋር አድርጎአልና ሕያው እግዚአብሔርን! ከራሱ ጠጕር አንዲት በምድር ላይ አትወድቅም” አሉት። ሕዝቡም ያን ጊዜ ስለ ዮናታን ጸለዩ፤ እርሱም አልተገደለም።