La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ቆሮንቶስ 6:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ይህ​ንም የም​ላ​ችሁ ስዘ​ል​ፋ​ችሁ ነው፤ እን​ግ​ዲህ ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸሁ ወን​ድ​ማ​ማ​ቾ​ችን ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ጋር ማስ​ታ​ረቅ የሚ​ችል ሽማ​ግሌ የለ​ምን?

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ይህንም የምለው ላሳፍራችሁ ብዬ ነው። ለመሆኑ በወንድሞች መካከል ለመፍረድ የሚበቃ ጠቢብ ሰው በመካከላችሁ የለምን?

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እንድታፍሩ ስል ይህን እላለሁ። ኧረ ለመሆኑ በወንድሞች መካከል ሽማግሌ ሊሆን የሚችል አንድ አስተዋይ ሰው አይገኝምን?

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ይህን የምለው እንድታፍሩ ብዬ ነው፤ ኧረ ለመሆኑ በወንድሞች መካከል ውሳኔ ለመስጠት የሚችል አስተዋይ ሽማግሌ አይገኝምን?

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አሳፍራችሁ ዘንድ ይህን እላለሁ። እንደዚህ ነውን? በወንድሞች መካከል ሽማግሌ ሊሆን የሚችል አንድ አስተዋይ ሰው በእናንተ ዘንድ አይገኝምን?

Ver Capítulo



1 ቆሮንቶስ 6:5
12 Referencias Cruzadas  

የዐዋቂዎች ጥበብ መንገዳቸውን ታውቃለች፤ የሰነፎች ስንፍና ግን ወደ ስሕተት ይመራል።


ያን​ጊ​ዜም ጴጥ​ሮስ ተነ​ሣና በወ​ን​ድ​ሞቹ መካ​ከል ቆመ፤ መቶ ሃያ ያህል ሰዎ​ችም በዚያ ሳሉ እን​ዲህ አላ​ቸው።


ሐና​ንያ ግን መልሶ እን​ዲህ አለ፥ “አቤቱ፥ ስለ​ዚህ ሰው በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በቅ​ዱ​ሳ​ኖ​ችህ ላይ የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ውን ክፉ ነገር ሁሉ ከብዙ ሰዎች ሰም​ቻ​ለሁ።


ተፈ​ጥ​ሮ​ዋስ አያ​ስ​ረ​ዳ​ች​ሁ​ምን? ወንድ ግን ጠጕ​ሩን ቢያ​ሳ​ድግ ነውር ነው።


ለጽ​ድቅ ትጉ፤ አት​ሳቱ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የማ​ያ​ው​ቁት ሰዎች አሉና፤ ነገር ግን እን​ድ​ታ​ፍሩ ይህን እላ​ች​ኋ​ለሁ፤


ራሳ​ች​ሁን አታ​ስቱ፤ ከመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ በዚህ ዓለም ጥበ​በኛ እንደ ሆነ የሚ​ያ​ስብ ሰው ጥበ​በኛ ይሆን ዘንድ ራሱን ዐላ​ዋቂ ያድ​ርግ።


እኛስ ስለ ክር​ስ​ቶስ ብለን አላ​ዋ​ቂ​ዎች ነን፤ እና​ንተ ግን በክ​ር​ስ​ቶስ ጠቢ​ባን ናችሁ፤ እኛ ደካ​ሞች ነን፤ እና​ንተ ግን ብር​ቱ​ዎች ናችሁ፤ እና​ንተ ክቡ​ራን ናችሁ፤ እኛ ግን የተ​ዋ​ረ​ድን ነን።


ይህ​ንም የጻ​ፍ​ሁ​ላ​ችሁ ላሳ​ፍ​ራ​ችሁ አይ​ደ​ለም፤ ልጆ​ችና ወዳ​ጆች እንደ መሆ​ና​ችሁ ልመ​ክ​ራ​ች​ሁና ላስ​ተ​ም​ራ​ችሁ ነው እንጂ፤ እኔ ለሁ​ላ​ችሁ ቤዛ​ችሁ ነኝ፤ እና​ንተ ግን አላ​ፈ​ራ​ች​ሁ​ኝም።


እን​ግ​ዲህ በሚ​ነ​ቅፉ ሰዎች ዘንድ ልት​ከ​ራ​ከሩ አት​ድ​ፈሩ፤ ከጓ​ደ​ኛው ጋር በዐ​መ​ፀ​ኞች ዘንድ ሊከ​ራ​ከር የሚ​ችል አለን? በደ​ጋ​ጎች ዘንድ አይ​ደ​ለ​ምን? ከባ​ል​ን​ጀ​ራው ጋር ክር​ክር ያለው ቢኖ​ርም በቅ​ዱ​ሳን ዘንድ ይከ​ራ​ከር፤ በሚ​ነ​ቅ​ፉና በዐ​መ​ፀ​ኞች ዘንድ ግን አይ​ደ​ለም።


ነገር ግን የዚህ ዓለም ክር​ክር ያላ​ቸው ሰዎች ቢኖሩ በቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን የተ​ሾሙ የበ​ታች ወን​ድ​ሞች ይስ​ሙ​አ​ቸው።


ከእናንተ ግን ማንም ጥበብ ቢጎድለው፥ ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉ የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን፤ ለእርሱም ይሰጠዋል።