La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ቆሮንቶስ 6:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በሆ​ነው ሁሉ ላይ ሥል​ጣን አለኝ፤ ግን ሁሉ የሚ​ጠ​ቅ​መኝ አይ​ደ​ለም፤ ሁሉም ይቻ​ለ​ኛል፤ ነገር ግን በእኔ ላይ እን​ዲ​ሠ​ለ​ጥን የማ​ደ​ር​ገው ምንም የለም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“ሁሉ ነገር ተፈቅዶልኛል፤” ይሁን እንጂ ሁሉም ነገር አይጠቅምም፤ “ሁሉ ነገር ተፈቅዶልኛል፤” ይሁን እንጂ ምንም ነገር በእኔ ላይ አይሠለጥንም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

“ሁሉ ተፈቅዶልኛል፤” ሁሉ ግን አይጠቅምም። ሁሉ ተፈቅዶልኛል፤ በእኔ ላይ ግን አንድ ነገር እንኳ አይሠለጥንብኝም።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“ሁሉ ነገር ተፈቅዶልኛል፤” ግን ሁሉም ነገር ይጠቅመኛል ማለት አይደለም፤ ሁሉም ነገር ተፈቅዶልኛል፤ ይሁን እንጂ ለማናቸውም ነገር ባሪያ ሆኜ አልገዛም፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሁሉ ተፈቅዶልኛል፥ ሁሉ ግን አይጠቅምም። ሁሉ ተፈቅዶልኛል፥ በእኔ ላይ ግን አንድ ነገር እንኳ አይሠለጥንብኝም።

Ver Capítulo



1 ቆሮንቶስ 6:12
12 Referencias Cruzadas  

ሴት ፈሳሽ ከአ​ለ​በት ወንድ ጋር ብት​ገ​ናኝ ሁለ​ቱም በውኃ ይታ​ጠ​ባሉ፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩ​ሳን ናቸው።


አይ​ሁ​ድም የዳ​ነ​ውን ሰው፥ “ዛሬ ሰን​በት ነው፤ አል​ጋ​ህን ልት​ሸ​ከም አይ​ገ​ባ​ህም” አሉት።


የኦ​ሪት ሕግ መን​ፈ​ሳዊ እንደ ሆነ እና​ው​ቃ​ለን፤ እኔ ግን ለኀ​ጢ​አት የተ​ሸ​ጥሁ ሥጋዊ ነኝ።


ለጣ​ዖ​ታት የተ​ሠ​ዋ​ውን ስለ​መ​ብ​ላት ግን ጣዖት ሁሉ በዓ​ለም ከንቱ እን​ደ​ሆነ፥ ከአ​ንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በቀር ሌላ አም​ላክ እን​ደ​ሌለ እና​ው​ቃ​ለን።


በእኛ ሹመት ሌላ የሚ​ቀ​ድ​መን ከሆነ የሚ​ሻ​ላ​ች​ሁን እና​ንተ ታው​ቃ​ላ​ችሁ፤ እኔ ይህን አል​ፈ​ለ​ግ​ሁ​ትም፤ ነገር ግን የክ​ር​ስ​ቶ​ስን ትም​ህ​ርት እን​ዳ​ላ​ሰ​ና​ክል በሁሉ እታ​ገ​ሣ​ለሁ።


ነገር ግን ለሌላ ሳስ​ተ​ምር፥ እኔ ለራሴ የተ​ና​ቅሁ እን​ዳ​ል​ሆን ሰው​ነ​ቴን አስ​ጨ​ን​ቃ​ታ​ለሁ፥ ሥጋ​ዬ​ንም አስ​ገ​ዛ​ዋ​ለሁ።


ይህም እኛን ልትመስሉ ራሳችንን እንደ ምሳሌ እንሰጣችሁ ዘንድ ነበር እንጂ፥ ያለ ሥልጣን ስለ ሆንን አይደለም።


እነዚህ ከእናንተ ጋር ሲጋበዙ በፍቅር ግብዣችሁ እንደ እድፍ ናቸው፤ እንደ እረኞች ያለ ፍርሃት ራሳቸውን ይጠብቃሉ፤ በነፋስ የተወሰዱ ውሃ የሌለባቸው ደመናዎች፥ ፍሬ የማያፈሩ ሁለት ጊዜ የሞቱ ከነሥራቸው የተነቀሉ በበጋ የደረቁ ዛፎች፥